የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
1. ይሁን እንዳሻው (አርባምንጭ ከተማ) ቅዳሜ ጥቅምት 29 2018 ዓ.ም, ክለቡ ከ ኢትዮጵያ መድን ጋር ባደረገው የ5ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 5ዐ ኛ ደቂቃ ላይሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀማቸው በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ። ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ የየውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
2. ክፍሎም ገ/ሂወት (ምድረ ገነት ሽረ ) ቅዳሜ ጥቅምት 29 2018 ዓ.ም. ክለቡ ከ ሲዳማ ቡና ጋር ባደረገው የ5ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 65 ኛ ደቂቃ ላይሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀማቸው በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ። ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ የየውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
3. በፍቃዱ አለማየሁ (ኢትዮጵያ ቡና) እሁድ ጥቅምት 30 2018 ዓ.ም. ክለቡ ከ አዳማ ከተማ ጋር ባደረገው የ5ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 74 ኛ ደቂቃ ላይሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀማቸው በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ። ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ የየውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
- ማሰታውቂያ -
4. ዳንኤል ፀሀይ (ምድረ ገነት ሽረ ) ከታች በተጠቀሱት ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ።
ግጥሚያ
- ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ ምድረ ገነት ሽረ
- ፋሲል ከነማ ከ ምድረ ገነት ሽረ
- ምድረ ገነት ሽረ ከ ሲዳማ ቡና
ስለሆነም የቡድን አመራሩ ለፈፀሙት ጥፋት በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ደንብ የውድድር ደንብ ክፍል 1 አንቀፅ 13 ንዑስ አንቀጽ 13.3 ተቁ 16 መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገዱ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 5ዐዐዐ /አምስት ሺ/ እንዲከፍሉ የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
5. አርባምንጭ ከተማ ክለቡ ከኢትዮጵያ መድን ጋር ባደረገው የ5 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የአርባምንጭ ከተማ ቡድን ተጫዋች የሆኑት
- ይሁን እንዳሻው 2*
- አማኑኤል ጎበና
- ፅዮን መርዕድ
- ፀጋዬ አበራ
በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 65 (ሀ) መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5ዐዐዐ / አምስት ሺ/ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡
6. ድሬደዋ ከተማ ክለቡ ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ጋር ባደረገው የ5 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የድሬደዋ ከተማ ቡድን ተጫዋች የሆኑት
- ሬድዋን ሸረፉ
- አቤል አሰበ
- ኣብ ካሳዬ
- ኣብዱሰላም ዩሱፍ
- ያሬድ ታደሰ
በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.አ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 65 (ሀ) መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 / አምስት ሺ / እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
7. ቅዱስ ጊዮርጊስ ክለቡ ከባህርዳር ከተማ ጋር ባደረገው የ5 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የቅዱስ ጊዮርጊስ ቡድን ተጫዋች የሆኑት
- ባይ ኩዊች
- ሀብታሙ ጉልላት
- አሚኑ ነስሩ
- ብሩክ ታረቀኝ
- ተገኑ ተሾመ
በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.አ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 65 (ሀ) መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 / አምስት ሺ /እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡
8. ምድረ ገነት ሽረ ክለቡ ከሲዳማ ቡና ጋር ባደረገው የ5 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የምድረ ገነት ሽረ ቡድን ተጫዋች የሆኑት
- ኣዲሱ ተስፋዬ
- ዳንኤል ዳርጌ
- ክፍሎም ገ/ሂወት 2*
- ዋልታ ዓንደይ
- ሄኖክ ተወልደ
- ሪችሞንድ አይ
- ተካልኝ ደጀኔ
በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 65 (ሀ) መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር አምስት ሺ /5000/እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡
9. አሰልጣኝ ዳንኤል ፀሀይ (ምድረ ገነት ሽረ ዋና አሰልጣኝ ) ክለቡ በ5ኛ ሳምንት መርሀ ግብር ያልተመዘገበ የቡድን አመራር በምክር መስጫ ሰለመገኘቱ ካርድ ስለመመልከቱ ሪፖርት ቀርቦበታል ። ስለሆነም ያልተመዘገበው የቡድን አመራር ለፈጸመው ጥፋት አሰልጣኙ ከላይ በተራ ቁጥር 4 ከተላለፈባቸው ቅጣት በተጨማሪ በፕሪምየር ሊግ ደንብ ክፍል 1 አንቀፅ 13.2 ተቁ 14 መሰረት 3/ሶስት/ ጨዋታ እንዲታገዱና ብር የ1ዐዐዐዐ/ አስር ሺህ/ እንዲከፍሉ የውድድርና ስነስር ወስኗል።


