የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
- ደግፌ አለሙ (ሲዳማ ቡና) ረቡዕ ጥቅምት 19 2018 ዓ.ም. ክለቡ ከ ፋሲል ከነማ ጋር ባደረገው የ3ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ ከጨዋታ በኋላ ዳኛን አፀያፊ ስድብ በመሳድብ በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ። ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 65 (ሀ) መሰረት 3 ጨዋታ እንዲታገድ ና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 3000 /ሶስት ሺህ/ እንዲከፍል የየውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
- ኢትዮ ኤሌትሪክ ክለቡ ከአርባምንጭ ከተማ ጋር ባደረገው የ3 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የኢትዮ ኤሌትሪክ ቡድን ተጫዋች የሆኑት
- በረከት ወልደዮሐንስ
- ሀሰን ሁሴን
- እዮብ ገ/ማርያም
- ሄኖክ ገብረህይወት
- ሙከረም ረሺድ
- አሸብር ተስፋዬ
በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 65 (ሀ) መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 / አምስት ሺ/ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡
- ማሰታውቂያ -

- ቅዱስ ጊዮርጊስ ክለቡ ከነገሌ አርሲ ጋር ባደረገው የ3 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የቅዱስ ጊዮርጊስ ቡድን ተጫዋች የሆኑት
- ቶሎሳ ንጉሴ
- ያብስራ ጎሳዬ
- አቤል ያለው
- ሄኖክ ዮሀንስ
- ሀብታሙ ጉልላት
በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 65 (ሀ) መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 / አምስት ሺ/ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡
- ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ክለቡ ከምድረ ገነት ሽረ ጋር ባደረገው የ3 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ቡድን ተጫዋች የሆኑት
- ሙሉአለም መስፍን
- ፍቃዱ መኮንን
- ብሩክ እንዳለ
- ዳዊት ገብሩ
- ኪሩቤል ወንድሙ
በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 65 (ሀ) መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 / አምስት ሺ/ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡
- ነገሌ አርሲ ክለቡ በ3ኛ ሳምንት መርሀ ግብር ቅድመ ጨዋታ ስብሰባ ላይ ስላለመገኘቱ ሪፖርት ቀርቦበታል። ስለሆነም ከለቡ ለፈጸመው ጥፋት በፕሪምየር ሊግ የውድድር ደንብ ክፍል 1 አንቀፅ 10 ተቁ 7 መሰረት ብር 5000/ አምስት ሺህ/ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።