የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
- ብሩክ እንዳለ (ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ) ቅዳሜ ጥቅምት 8 2018 ዓ.ም. ክለቡ ከ ሲዳማ ቡና ጋር ባደረገው የ1ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 90+2 ኛ ደቂቃ ላይ ሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀማቸው በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል። ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ የየውድድርና ስነስርዓት ከሚቴ ወስኗል።
- ኢብራሂም ዳንላንድ (ኢትዮጵያ ቡና) እሁድ ጥቅምት 9 2018 ዓ.ም. ክለቡ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ባደረገው የ1ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 60 ኛ ደቂቃ ላይ በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል። ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 63 በተቁ 1 (ሐ) እና በተቁ 2 መሰረት 3 ጨዋታ እንዲታገድ ና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 3000 /ሶስት ሺህ/ እንዲከፍል የየውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
- ኤልያስ አህመድ (ሀዲያ ሆሳዕና) ሰኞ ጥቅምት 10 2018 ዓ.ም. ክለቡ ከ ባህርዳር ከተማ ጋር ባደረገው የ1ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 54 ኛ ደቂቃ ላይ በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል። ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 63 በተቁ 1 (ለ) እና በተቁ 2 መሰረት 3 ጨዋታ እንዲታገድ ና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 3000 /ሶስት ሺህ/ እንዲከፍል የየውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
- ሐይደር ሸረፋ (አዳማ ከተማ) ሰኞ ጥቅምት 10 2018 ዓ.ም. ክለቡ ከ ኢትዮጵያ መድን ጋር ባደረገው የ1ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 74 ኛ ደቂቃ ላይ ሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀማቸው በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል። ስለሆነም ተጨዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ የየውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
1. ኢትዮጵያ ቡና ክለቡ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ባደረገው የ1 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የኢትዮጵያ ቡና ቡድን ተጫዋች የሆኑት
- አቡበከር አዳሙ
- ኦካይ ጁል
- ኢብራሂም ዳንላንድ
- ራምኬል ጀምስ
በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.አ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 65 (ሀ) መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 /አምስት ሺህ/ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
2. ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ክለቡ ከፋሲል ከነማ ጋር ባደረገው የ1 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቡድን ተጫዋች የሆኑት
- ማሰታውቂያ -
- በዛብህ ካቲሴ
- ዮናስ ለገሰ
- መላኩ አሊያስ
- አስጨናቂ ፀጋዬ
- አዲስ ግደይ
- ፓልክ ቾል
በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 65 (ሀ) መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 /አምስት ሺህ/ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
3. ሀዲያ ሆሳዕና ክለቡ ከባህርዳር ከተማ ጋር ባደረገው የ1 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የሀዲያ ሆሳዕና ቡድን ተጨዋች የሆኑት
- ኢዮብ አለማየሁ
- ኤልያስ አህመድ
- ብሩክ በየነ
- ሄኖክ አርፌጮ
- ቃለአብ ውብሸት
- ተስፋዬ ብርሀኑ
በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 65 (ሀ) መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 /አምስት ሺህ/ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
4. ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ክለቡ ከሲዳማ ቡና ጋር ባደረገው የ1 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የቡድኑ ተጫዋች የሆኑት ብሩክ እንዳለ እና ተስፋዬ ተስፋዬ
- ብሩክ እንዳለ
- ሰመረ ሃፍተይ
- ብሩክ እንዳለ
- ነፃነት ገ/መድህን
- ኪሩቤል ወንድሙ
በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 65 (ሀ) መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 /አምስት ሺህ/ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።


