የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
1. ማርቲን ኪዛ (ፋሲል ከነማ) : እሁድ ግንቦት 10 2017 ዓ.ም. ክለቡ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ባደረገው የ30ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 45+2 ኛ ደቂቃ ላይ ዳኛን አፀያፊ ስድብ በመሳድብ በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ። ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 66 በተቁ 1 መሰረት 3 ጨዋታ እንዲታገድ ና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 3000 /ሶስት ሺ/ እንዲከፍል የውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
2. ፈቃደስላሴ ደሳለኝ (ሃዋሳ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም ከታች በተጠቀሱት 4 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል ።
- ሀዲያ ሆሳዕና – ሃዋሳ ከተማ
- ሃዋሳ ከተማ – ድሬደዋ ከተማ
- ሀዋሳ ከተማ – ባህርዳር ከተማ
- ሃዋሳ ከተማ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
በመሆኑም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል ።
3. ሙሉጌታ ወ/ጊዮርጊስ (መቐለ 70 እንደርታ) : ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል ።
- ማሰታውቂያ -

- ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ – መቐለ 70 እንደርታ
- መቐለ 70 እንደርታ -አዳማ ከተማ
- መቐለ 70 እንደርታ -ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
- ወላይታ ድቻ – መቐለ 70 እንደርታ
- መቐለ 70 እንደርታ- ኢትዮጵያ መድን
በመሆኑም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ እፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል ።
4. አላዛር ማረነ (ድሬደዋ ከተማ) : ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል ።
- ባህርዳር ከተማ – ድሬደዋ ከተማ
- ኢትዮጵያ መድን – ድሬደዋ ከተማ
- አዳማ ከተማ – ድሬደዋ ከተማ
- ድሬደዋ ከተማ – ኢትዮ ኤሌትሪክ
- ድሬደዋ ከተማ – አርባምንጭ ከተማ
በመሆኑም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ እፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል ።
5. አስጨናቂ ፀጋዬ (ሀዲያ ሆሳዕና) : ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል ።
- ሀዲያ ሆሳዕና – ሲዳማ ቡና
- ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ-ሀዲያ ሆሳዕና
- ሀዲያ ሆሳዕና – ድሬደዋ ከተማ
- ኢትዮጵያ ቡና – ሀዲያ ሆሳዕና
- ሀዲያ ሆሳዕና – ስሁል ሽረ
በመሆኑም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ እ ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ
ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል ።
6. ሃዋሳ ከተማ : ክለቡ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ባደረገው የ30 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የሃዋሳ ከተማ ቡድን ተጫዋች የሆኑት
- ተባረክ ሔፋሞ
- ፈቃደስላሴ ደሳለኝ
- አሊ ሱሌማን
- አቤኔዘር ዮሐንስ
- እስራኤል እሸቱ
- በረከት ሳሙኤል
በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 /አምስት ሺ/ እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡
7. ሲዳማ ቡና: ክለቡ ከወላይታ ድቻ ጋር ባደረገው የ30 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የሲዳማ ቡና ቡድን ተጫዋች የሆኑት
1 ሐብታሙ ታደሰ
2 ረድዋን ናስር
3 ፍቅረየሱስ ተ/ብርሀን
4 ጊት ጋትኩት
5 ደስታ ደሙ
6 አቤኔዘር አስፋው
በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ እፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 /አምስት ሺ/ እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡
8. ፋሲል ከነማ : ክለቡ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ባደረገው የ30 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የፋሲል ከነማ ቡድን ተጫዋች የሆኑት
- ማርቲን ኪዛ
- ጌታነህ ከበደ
- ማርቲን ኪዛ
- በረከት ግዛው
- ኤፍሬም ሀይሉ
- እዮብ ማቲያስ
- ዳንኤል ፍፁም
በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 /አምስት ሺ/ እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡
9. አሰልጣኝ ጎይቶም ኃይለ (ረዳት አሰልጣኝ) መቐለ 70 እንደርታ : ክለቡ ከኢትዮጵያ መድንጋር በነበረው የ30ኛ ሳምንት እግር ኳስ ጨዋታ በውድድር አመቱ ውስጥ ለሶስተኛ ጊዜ ቢጫ ካርድ ተመልክተዋል። ስለሆነም በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ደንብ ክፍል 1 አንቀፅ 13 በተቁ 35 መሠረት አሰልጣኙ 1/አንድ ጨዋታ እንዲታገዱና ብር / 5000 /አምስት ሺህ / እንዲከፍሉ ወስኗል።


