የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
1. ኢያሱ ደስታ (ሀዲያ ሆሳዕና) : ማከሰኞ ግንቦት 5 2017 ዓ.ም. ክለባቸው ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ጋር ባደረገው የ29ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 89 ኛ ደቂቃ ላይ የተጋጣሚን ቡድን አፀያፊ ስድብ በመሳድብ በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገዱ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦባቸዋል ። ስለሆነም የቡድን አመራሩ ለፈፀሙት ጥፋት በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ደንብ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 66 በተቁ 1 መሰረት 3 ጨዋታ እንዲታገዱ ና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 10000 /አስር ሺ/ እንዲከፍሉ የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
2. ናትናኤል ናሴሮ (ወላይታ ድቻ) : ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል ።
- ድሬደዋ ከተማ – ወላይታ ድቻ
- ወላይታ ድቻ -ሲዳማ ቡና
- አዳማ ከተማ – ወላይታ ድቻ
- ወላይታ ድቻ – አርባምንጭ ከተማ
- ኢትዮጵያ ቡና – ወላይታ ድቻ
በመሆኑም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል ።
3. ዳዋ ሆጤሳ (ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ) : ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል ።
- ማሰታውቂያ -

- ፋሲል ከነማ – ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ
- ኢትዮጵያ ቡና – ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ
- ሃዋሳ ከተማ – ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ
- ኢትዮ ኤሌትሪክ – ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ
- ሀዲያ ሆሳዕና – ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ
በመሆኑም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል ።
4. ብሩክ እንዳለ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ) : ከታች በተጠቀሱት 10 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል ።
- መቻል – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
- ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ – ኢትዮጵያ መድን
- ሲዳማ ቡና – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
- ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ – ኢትዮ ኤሌትሪክ
- ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ – ስሁል ሽረ
- ስሁል ሽረ – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
- ኢትዮጵያ መድን – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
- ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ – ሲዳማ ቡና
- ሃዋሳ ከተማ – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
- ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ-ባህርዳር ከተማ
በመሆኑም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ እ ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 35(ሠ) መሰረት 2 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 2000 እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል ።
5. ፍሪምፖንግ ሜንሱ (መቻል) :በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 2 እንዲሁም ከታች በተጠቀሱት 3 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል ።
- መቻል – ቅዱስ ጊዮርጊስ
- መቻል – አርባምንጭ ከተማ
- መቻል – ስሁል ሽረ
በመሆኑም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል ።
6. አሰልጣኝ መስፍን ነጋሽ (የግብ ጠባቂአሰልጣኝ አዳማ ከተማ) : ክለቡ ከ መቐለ 70 እንደርታ ጋር በነበረው የ28ኛ ሳምንት እግር ኳስ ጨዋታ በውድድርአመቱ ውስጥ ለሶስተኛ ጊዜ ቢጫ ካርድ ተመልክተዋል። ስለሆነም በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ደንብ ክፍል 1 አንቀፅ 13 በተቁ 35 መሠረት አሰልጣኙ 1/አንድ ጨዋታ እንዲታገዱና ብር / 5000 /አምስት ሺህ / እንዲከፍሉ ወስኗል።
7. አሰልጣኝ ነፃነት ክብሬ (ዋና አሰልጣኝ) : ኢትዮጵያ ቡና ክለቡ ከ ወላይታ ድቻጋር በነበረው የ29ኛ ሳምንት እግር ኳስ ጨዋታ በውድድር አመቱ ውስጥ ለሶስተኛ ጊዜ ቢጫ ካርድ ተመልክተዋል። ስለሆነም በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ደንብ ክፍል 1 አንቀፅ 13 በተቁ 35 መሠረት አሰልጣኙ 1 አንድ ጨዋታ እንዲታገዱና ብር / 5000 /አምስት ሺህ / እንዲከፍሉ ወስኗል።
ጥሪ
አሰልጣኝ በረከት ደሙ(ዋና አሰልጣኝ) እና አሰልጣኝ ገረሱ ሽመና ረዳት አሰልጣኝ /አርባ ምንጭ ከተማ/ የፕሪምየር ሊግ ውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ሊያነጋግራችሁ ስለሚፈልግ ሀሙስ ግንቦት 7 2017 በ 09:30 ስዓት ታደሰ ኢንጆሪ ሆቴል (ቅድመ ስብሰባ በሚደረግት ቦታ) እንድትገኙ ጥሪውን ያስተላልፋል።


