የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
1. ብሩክ ባይሳ (አርባምንጭ ከተማ): ሐሙስ ሚያዝያ 2 2017 ዓ.ም. ክለቡ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ባደረገው የ24ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 85 ኛ ደቂቃ ላይ ሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀሙ በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ። ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
2. ፋሃድ አዚዝ (ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ) : ሰኞ መጋቢት 29 2017 ዓ.ም. ክለቡ ከኢትዮጵያ መድን ጋር ባደረገው የ24ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 69 ኛ ደቂቃ ላይ ሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀሙ በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ። ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ እፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ የ ውድድርአመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።

- ማሰታውቂያ -
3. ኢትዮጵያ ቡና ክለቡ ከባህር ዳር ከተማጋር በነበረው የ24ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ ግጥሚያው 3 ደቂቃ ዘግይቶ ለመጀመሩ ምክኒያት እንደነበረ ሪፖርት ቀርቦበታል ።
በመሆኑም በፕሪምየር ሊግ የውድድር ደንብ ክፍል 1 አንቀፅ 13 ንዑስ አንቀፅ 13.2 ተቁ 17 መሰረት ከለቡ ብር 15000/አስራ አምስት ሺህ/ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።


