የአፍሪካ ኮንፌደሬሽን ዋንጫ የመልስ ጨዋታዎች በነገው ዕለት ሲደረጉ ካይሮ ላይ የግብፁ ዛማሊክ የደቡብ አፍሪካውን ስቴሌንቦሽን ያስተናግዳል።
በካይሮ ኢንተርናሽናል ስታድየም የሚደረገውን ጨዋታ ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተሰማ በዋና ዳኝነት ይመሩታል።
ባምላክ ተሰማ በወድድር ዘመኑ የሚመሩት ሶስተኛ የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ጨዋታ ሲሆን ቀደም ብለው ስታድ ማልየን ከቤርካኔ እንዲሁም ብላክ ፑልስ ከኢንዬምባ ያደረጓቸውን ጨዋታዎችን መርተዋል።
በተጨማሪም ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ቴዎድሮስ ምትኩ በአራተኛ ዳኝነት የተሰየሙ ሲሆን ቡርኪናቤው ሰይዱ ትያማ እና የጅቡቲ ዜግነት ያለው ሊባን አህመድ በረዳት ዳኝነት ጨዋታውን ይመራሉ።
- ማሰታውቂያ -
ጨዋታው ነገ ከአመሻሽ 12:00 ጀምሮ የሚደረግ ሲሆን የመጀመሪያው ዙር ጨዋታ 0 ለ 0 ተጠናቋል።


