የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
1. ሙሳ ራመታን (ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ) : ክለቡ ከወላይታ ድቻ ጋር ባደረገው የ22ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 90+6 ኛ ደቂቃ ላይ የተጋጣሚን ቡድን ግልፅ ግብ የማግባት ዕድል በማበላሸት በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ። ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 63 በተቁ 1 (ሐ) እና በተቁ 2 መሰረት 3 ጨዋታ እንዲታገድ ና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 3000 /ሶስት ሺ/ እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
2. ዲቫይን ዋቹኩዋ (ኢትዮጵያ ቡና) : ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል ።
- ሀዲያ ሆሳዕና – ኢትዮጵያ ቡና
- ኢትዮጵያ ቡና – ባህር ዳር ከተማ
- ኢትዮጵያ ቡና – መቻል
- ስሁል ሽረ – ኢትዮጵያ ቡና
- ሃዋሳ ከተማ – ኢትዮጵያ ቡና
በመሆኑም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ እ‥ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል ።
- ማሰታውቂያ -
3. ቢኒያም ካሣሁን (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) : ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል ።
- ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
- መቻል – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ – መቀሌ 70 እንደርታ
- ሲዳማ ቡና – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
- ኢትዮጵያ መድን – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
በመሆኑም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በ ኢ እ‥ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል ።


