የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
1. አሸናፊ ፊዳ (አርባምንጭ ከተማ) : ማከሰኞ ጥር 27 2017 ዓ.ም. ክለቡ ከሀዲያ ሆሳዕና ጋር ባደረገው የ18ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 62 ኛ ደቂቃ ላይ የተጋጣሚን ተጫዋች በመማታት በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ። ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 63 በተቁ 1 (ሠ) እና በተቁ 2 መሰረት 4 ጨዋታ እንዲታገድ ና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 3000 /ሶስት ሺ/ እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።
2. ወንድማገኝ ማዕረግ (ሃዋሳ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም ከታች በተጠቀሱት 4 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል ።
- ሀዲያ ሆሳዕና – ሃዋሳ ከተማ
- ወላይታ ድቻ – ሃዋሳ ከተማ
- ሃዋሳ ከተማ – መቻል
- ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ – ሃዋሳ ከተማ
በመሆኑም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል ።
- ማሰታውቂያ -

3. ይሁን እንዳሻው (አርባምንጭ ከተማ) : ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል ።
- ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ – አርባምንጭ ከተማ
- አርባምንጭ ከተማ – ድሬደዋ ከተማ
- ፋሲል ከነማ – አርባምንጭ ከተማ
- ኢትዮጵያ ቡና – አርባምንጭ ከተማ
- አርባምንጭ ከተማ – ሀዲያ ሆሳዕና
በመሆኑም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ እ‥ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 /አንድ ሺ አምስት መቶ/ እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል ።
4. ነፃነት ገብረመድህን (ስሁል ሽረ) : ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል ።
- ወላይታ ድቻ – ስሁል ሽረ
- ኢትዮጵያ ቡና – ስሁል ሽረ
- ስሁል ሽረ-ባህርዳር ከተማ
- ስሁል ሽረ-መቻል
- ሲዳማ ቡና – ስሁል ሽረ
በመሆኑም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 /አንድ ሺ አምስት መቶ/ እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል ።
1. ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ክለቡ ከድሬደዋ ከተማ ጋር ባደረገው የ18 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ቡድን ተጫዋች የሆኑት
- ናትናኤል ሰለሞን
- ቡልቻ ሹራ
- ጋዲሳ መብራቴ
- ሳምሶን ጥላሁን
- ሱልጣን በርሄ
- በረከት አማረ
በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 /አምስት ሺ/ እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ- ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡
2. ወላይታ ድቻ ክለቡ ከመቐለ 70 እንደርታ ጋር ባደረገው የ18 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የወላይታ ድቻ ቡድን ተጫዋች የሆኑት
- ፍጹም ግርማ
- አብነት ደምሴ
- ብዙአየሁ ሰይፉ
- ውብሸት ክፍሌ
- ቢኒያም ገነቱ
በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 /አምስት ሺ እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ- ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡
3. አዳማ ከተማ ክለቡ ከ ኢትዮ ኤሌትሪክ ጋር በነበረው የ18ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ ቅድመ ስብሰባ ወቅት የክለቡ ተወካይ ስላለመምጣቱ ሪፖርት ቀርቦበታል ። በመሆኑም በፕሪምየር ሊግ የውድድር ደንብ ክፍል 1 አንቀፅ 10 ተቁ 8 መሰረት ከለቡ ብር 5000/አምስት ሺህ/ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።


