የድሬዳዋ ከተማ ስፖርት ክለብ ሶስት ወጣቶችን ወደ ዋናው ቡድን አሳደገ።

ክለቡ ሶስት ካሳደጋቸው ወጣቶች የኃላ መስመር ተጫዋች የሆነውን ሚኪያስ ካሳሁን ከ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ተስፈ ቡድን የተገኘ ሲሆን ሁለቱ አምና የድሬ ከተማ ከ20 ዓመት በታች ቡድን ሲጫወቱ የነበሩ ሲያም ሱልጣንና አቢዩ ካሳዬም ለሶስት ዓመታት በክለቡ ለመቆየት ፊርማቸውን አኑረዋል።

አምና በኤም አር አይ ምርመራ የተጫዋች እጥረት ምክንያት ከ20 ዓመት በታች ቡድን ያለቦታው ሲያገለግል የነበረው ቁመተ ለግላጋው የተከላካይ አማካይ ስፍራ ተጫዋች ሲያም ሱልጣን ባለፉት ሳምንታት ለአቶ ሻውል ሐይሌ የህክምና ገቢ መሰብሰቢያ ውድድር ላይ ማራኪ እንቅስቃሴ በማድረግ የቡዙዎችን ቀልብ መሳብ ችሏል። በለገሐሬ አስታጥቄ ሜይዳ እግር ኳስን መጫወት የጀመረው ሲያም ከ U-17 ጀምሮ በድሬዳዋ ከተማ ቆይታ እያደረገ ይገኛል።

አምና በተመሳሳይ ለተስፈ ቡድን ሲጫወት የነበረው ግብ ጠባቂ አቢዩ ካሳዬ ለሶስት ዓመታት በክለቡ ለመቆየት ፈርሟል።
ከጎሮ ሰፈር የተገኘው ግብ ጠባቂ አቢዩ በድሬዳዋ ከፍተኛ ዲቪዚዮን ለዋሊያ በመጫወት አሳልፏል።
በመሃል ተከላካይ ስፍራ የሚጫወተው ሚኪያስ ካሳሁን ከፕሮጀክት ጀምሮ እግር ኳስ መጫወት የጀመረ ሲሆን አምና ለቅዱስ ጊዮርጊስ ተስፈ ቡድን በመጫት ማሳለፍ ችሏል።
የድሬዳዋ ከተማ ስፖርት ክለብ ለታዳጊዎች ልዩ ትኩረት በመስጠት እየተንቀሳቀሰ የሚገኝ ሲሆን ከ25 በታች ቡድን ለማቋቋም ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል።

Via – dire kenema official

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook

hatricksport team

Hatricksport team