በውይይቱ ላይ አቶ በላይ ደጀን የአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ እና መቶ ሀለቃ ፍቃደ ማሞ የሊግ ካምፖኒ የቦርድ ሀላፊ ንግግር አደረጉ
ሁለቱም ቡድኖች የማይተካ ሚና ያላቹ እና የ አዲስ አበባ ድምቀቶች ናችሁ በማለት ንግግራቸውን የጀመሩት አቶ በላይ የአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ እንደሚያከብራች ገልፀዋል

በህዳሴው ዋንጫ ዛሬ በሚደረገው ጨዋታ ታሪክ በመስራት እግር ኳስ በአዲስ አበባ እንድትደምቅ ታደርጋለችሁ ብለዋል ።
- ማሰታውቂያ -
አብሮነታችሁን የሚነጣጠሉ ነገሮችን ከራሳችሁ አርቁ እግር ኳስ ከ ፖለቲካ ፣ብሄር፣ ጉጠኝነት ፈፅሞ እንዳይኖር አድርጉ ።
በፌስቡክ ፣ ቲክቶ አንዱን ከሌላ ለማጋጨች የሚደረጉ ፖለቲካ ይዘት ያለቸውን የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ሰለባ እንዲሆን እንደማይፈልጉ ገልፀዋል ።
መታረም ያለባቸው ጉዳዮች :- ወንበር መስበር : በእረፍት ሰዓት አሺሽ ሚጠቀሙ ረባሾችን ማጥራት አለባችሁ ። መጨረሻም ለሁለቱም ቡድኖች የመልካም ውጤት ምኞት በመኘት ንግግራቸውን ቋጭተዋል ።
”መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ የሊግ ካምፓኒ የቦርድ ዋና ሀላፊ ”

የሁለቱ ቡድን ቁልፍ ደጋፊዎች ሀላፊነት ይጠበቅባችዋል : ሊጉ ከ 6 ዓመት በዋል ወደ መዲናዋ ይመጣል በመሆኑም በሁለታቹሁም በኩል የሚጠበቁ ብዙ ስራ መስራት አለባችሁ በሚገባ ። ስታዲየም ውስጥ ዋላ ቀር ስደቦች አስፈላጊ እንዳለሆነ እና እነዛን የወረዱ የዘቀጡ ስራዎች እንዳናርግ መጠንቀቅ አለብን ::
ብዙ ዋጋ ከፍለናል ሊጉ ወደዚህ እንዲመጣ ሀደራ ሊጉን በድጋሚ እንዳናርቀው በማለት ንግግራቸውን ጨርሰዋል ።
አቶ በላይ ከ ሁሉቱ ቡድን ደጋፊዎች ጋር በአሁኑ ሰዓት ውይይት እያደረጉ ይገኛሉ ።
የህዳሴ ዋንጫ በ ዛሬው እለት በሸገር ደርቢ ከ ዘጠኝ ሰዓት ተኩል የሚደረግ ይሆናሉ ።


