አሰልጣኝ ፍሰሐ ጥዑመልሳን በድሬድዋ ይቆያሉ
በዘንድሮው የቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ አነጋጋሪ አስተያየቶችን በመስጠት በስፖርት ተመልካቹ ዘንድ እይታን ያገኙት ፍሰሐ ጥዑመልሳን በድሬድዋ ከተማ ቤት እንደሚቆዩ አረጋግጠውልናል ።
ከአሰልጣኝ ፍሰሐ ጥዑመልሳን ጋር ባደረግነው ቆይታ ከክለቡ ሀላፊዎች ጋር በወቅታዊ የክለቡ ጉዳዮች ላይ መነጋገራቸው እና የመጀመሪያ ማስጠንቀቂያ ከክለቡ እንደተሰጣቸው ገልፀውልናል ።
ከዚህ በተጨማሪም ከድሬደዋ ከተማ ጋር እንደሚቀጥሉ አስረግጠው ሲናገሩ በዛሬው ዕለት የመጀመሪያ ልምምድ ማሰራታቸውን ገልፀውልናል ።
ድሬደዋ ከተማ በቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር በ አስራ አንድ ጨዋታዎች አስር ነጥቦችን ሰብስበው አስራ አንደኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠው ይገኛሉ ።