” ከአቡበከር ናስር ውጪ ለእኔ ምርጥ ተጫዋች የለም “ሚኪያስ መኮነን /ኢትዮጵያ ቡና/

የእግር ኳስ ህይወቱን ከሰፈር ፕሮጀክት አንድ ብሎ በመጀመር በ ሀረር ሲቲ የታዳጊ ቡድን ውስጥ አልፎ ከ ኢትዮጵያ ቡና ታዳጊ ቡድን እስከ ዋናው ቡድን በተሰለፈባቸው ጨዋታዎች አመርቂ ብቃቱን እያሳየ ይገኛል ።

ተስፈኛው የመስመር አጥቂ ሚኪያስ መኮንን ከ 2009 የውድድር ዓመት አንስቶ በ ኢትዮጵያ ቡና አስገራሚ ብቃቱን እያሳየ ሲቆይ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከ ሀትሪክ ስፖርት ፀሀፊ ቅዱስ ዮፍታሔ ጋር ቆይታን ማድረግ ችሏል ።

የኢትዮጵያ ቡና ጉዞው እና በቀጣይ . . . . . . . .

ለእኔ በጣም ጥሩ ነው ከአምናው የተሻለ ነገር ነው ያለው በውጤት እንዲሁም በአጨዋወት ወጥ የሆነ ቡድን ይዘናል ። በመጪው መርሐ ግብሮች  ባህርዳር ላይም የተሻለ ነገር እናሳየለን ብዬ አስባለው ፣ የመጫወቻ ሜዳውም ቢሆን ለቡድናችን አጫዋወት ጥሩ ነው ብዬ አስባለው ።

ቡድናችን በዘንድሮው የውድድር ዓመት ብዙ ጥሩ ጎን አሉት ፣ ከሌላ ቡድን በተለየ መልኩ የራሱ የሆነ የአጨዋወት ያለው ይህንንም በደንብ ከጨዋታ ጨዋታ በደንብ እያሻሻልን ነው ። ሌላው ዋነኛው ደግሞ ሸገር ደርቢን ጨምሮ ትላልቅ የሚባሉትን ቡድኖች አሳምኖ ማሸነፉ ነው ። የቡድናችን ድክምት ብዬ የማስበው ውጤትን አስጠብቆ አለመውጣታችን እና በእያንዳንዱ ጨዋታ በራሳችን ስህተቶች ግቡ ይቆጠርብናል ይህ ክፍተታችን ሲሆን የምንቀርፈው ይሆናል ።

ስለ ሊጉ ፉክክር . . . . . . . .

የዘንድሮው የውድድር ዓመት ብርቱ ፉክክር የሚታይበት እና የነጥብ መቀራረቦች ያሉበት ሲሆን ለተመልካቹ ደስ የሚል ነገር ቢሆንም ከሁለተኛው ዙር በኋላ ግን እንደዚህ የሚቀጥል አይመስለኝም ። ሁለት ወይም ሶስት ቡድኖች ተነጥለው በውጣት ነጥቡን የሚያሰፉት ይመስለኛል ።

ስለ ውጭ ሀገር አሰልጣኞች እና አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ . . . . . . .

በብዙ የውጪ አሰልጣኞች ለመሰልጠን ችያለው ነገር ግን ብዙም የተለየ ነገር የላቸውም ። እንደውም አንዳንዶቹ አሰልጣኞቹ ለእኔ ብቃታቸው አይታየኝም ፣ ልዩነቱ የአስተሳሰብ ብቻ መስሎ ሲሰማኝ የሀገራችን አሰልጣኞች የተሻሉ ናቸው ።

በካሳዬ ስር መሰልጠን በጣም ትልቅ ነገር ነው ፣ አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ ለ ኢትዮጵያ እግር ኳስ የራሱን ሀሳብ ይዞ መጥቶ ጥሩ ነገር እየሰራ ይገኛል ። ይሄ ነገር ደግሞ ከ አንድ ወይም ሁለት ዓመት በኋላ ከዚህ የተሻለ ፍሬያማ የሚሆን ይመስለኛል ።

አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ በጣም ጥሩ ሰው ነው ፣ ሁሌም መልካም ነገርን ያስባል እኔን አሁን ስለሚያሰለጥኝን አይደለም ይህን የምናገረው እውነታው ስለሆነ እና አቅም ያለው ትልቅ አሰልጣኝ ስለሆነ ነው ።

የሚኪያስ መኮንን ምርጦች . . . . .

በእስካሁኑ የእግር ኳስ ህይወቴ በታዳጊ ውድድር ላይ ሀገሬን ወክዬ ግብፅ ላይ ያስቆጠርኩት ጎል የእኔ ምርጡ ጎል ነው ። ሁሌም ስመለከተው እንደ አዲስ ደስታ የሚሰማኝ ከዚህ ባለፈ ግን ለእኔ በዚህ ሰዓት ምርጡ ተጫዋች አቡበከር ናስር ( አቡኪ ) ሲሆን ከእርሱ ውጪ ማንም የለም ።

በቀጣይ . . . . . . .

ዘንድሮ ከ ድሬደዋ ጋር ስንጫወት ከተጎዳሁ በኋላ ቡድኔን በጉዳት ምክንያት ማገልገል አልቻልኩም ። በጣም አንዶኛል በተለይም የሸገር ደርቢ ያሸነፈው ቡደን ላይ ባለመኖሬ በጣም ተከፍቼ ነበር ። በቀጣይ በደንብ አገግሜ በሙሉ አቋሜ ኢትዮጵያ ቡናን በደንብ ለማገልገል ጠንክሬ እሰራለው ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *