” ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ማሊያ ውጪ አልለብስም”
አሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛው
ውጤታማው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች ቡድን አሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛው ለተጨማሪ ሁለት አመታት የሚያቆየውን ኮንትራት አራዘመ።
ባለፉት 14 አመታት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቆይታው 16 ዋንጫ ያነሳው አሰልጣኙ ባለፉት አምስት አመታት የሊጉን ዋንጫ ያሸነፈ ሲሆን አምስቴ ባለፈበት የሴካፋ ሻምፒዮና በመወዳደርም ባለ ታሪክ ነው።
አሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛው ከፊርማው በኋላ “በምወደው ክለብ ኮንትራቴን በማራወሜ ደስተኛ ነኝ በቀጣይ አመታት ትልቅ አደራ መሸከሜን ተረድቻለሁ ንግድ ባንክን ከዚህ በላይ ከፍ ለማድረግ እጥራሁ” ሲል ተናግሯል።
- ማሰታውቂያ -
አሰልጣኙ “ለክለቤ ትልቅ ፍቅር አለኝ ታማኝነቴ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነው ወደፊትም ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ማሊያ ውጪ አልለብስም” ሲል አሰተያየቱን ሰጥቷል።


