በትላንትናው እለት ህክምናቸውን በመጨረስ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በመቅረብ ፍርማቸውን ካስቀመጡ መካከል የመጀመሪያዋ ምርቃት ፈለቀ ስትሆን ምርቃት በ ዘንድሮ የውድድር ዓመት በአንደኛው ዙር በግሏ ለአርባምንጭ ከፍተኛ እንቅስቃሴ ስታደርግ የነበረች ሲሆን በሁለተኛ ዙር ወደ ከፍተኛ ሊግ የወረደው ቂርቆስ ክ / ከተማን መቀላቀል ችላለች ። ምርቃት በ ብርሀኑ ግዛ ቡድን ለሁለት ዓመት ለመቆየት በወር ያልተጣራ ወራዊ ደሞዝ 204,310.00 ፍርማዋን አኑራለች ።
ሁለተኛ ፈራሚዋ ሰላማዊት ጎሳዬ በሀዋሳ ከተማ በተለይም በዘንድሮ ዓመት የንግድ ባንክ ከፍተኛ ተፎካካሪ በነበርው ቡድን ከፍተኛ እንቅስቃሴ ስታደርግ የነበረች የአጥቂ ስፍራ ተጫዋቾች ስትሆን ለቀጣዮቹ ሁለት ዓመት በንግድ ባንክ ለመቆየት በወር 204,310.00 ያልተጣራ የሚከፈላት ይሆናል ።
በተመሳሳይ ሁለቱ የ ሀዋሳ ከተማ ጥንካሬ የነበሩት እፀገነት ግርማ እሙሽ ዳንኤል በ 2018 ዓ.ም በ ካፍ ቻምፒየንስ ሊግ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተፎካካሪ ለማድረግ በሁለት ዓመት ውል አምርተዋል እያንዳዳቸውም ያልተጣራ 238,793 ብር የሚከፈላቸው ይሆናል ።
ሌላኛዋ የ ንግድ ባንክን የተከላካይ ስፍራ ለማጠናከር ፍርማዋን ያኖረችው ቤቴልሄም ግዛቸው ስትሆን በሴካፋ ዞን አሸናፊዎቹ ቤት ለሁለት ዓመት በወር ያልተጣራ ወራዊ ደሞዝ 195,689.00 የሚከፈላት ይሆናል ።
- ማሰታውቂያ -
የቡድኑ አምበል የናሽናል ቲሙ የረዥም ጊዜ ግብ ጠባቂ ከንግድ ባንክ ጋር በርካታ ዋንጫዎችን ከፍ አድርጋ ማንሳት የቻለችው ታሪኳ በርገነ በድጋሚ በንግድ ባንክ ማለያ ለመድመቅ ለሁለት ዓመት በወር ያልተጣራ ደሞዝ 214,931.00 እየተከፈላት ለመጫወት ፍርማዋን አኑራለች



