ለመጀመሪያ ጊዜ በሴቶች የአፍሪካ ሻምፒየንስ ሊግ ተሳታፊ የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሴቶች እግር ኳስ ክለብ ውድድሩ ወደ ሚካሄድበት ኬንያ ከማቅናታቸው አስቀድሞ በዛሬዉ ዕለት የሽኝት መርሀ ግብር ተደርጎላቸዋል።
በዋቢ ሸበሌ በተደረገው የሽኝት መርሐ ግብርም የባንኩ ዋና ፕሬዚዳንት፣የክለቡ ከፍተኛ ባለስልጣናት እና የኢትዮጵያ ደጋፊዎች ማህበር በስፍራው በመገኘት ቡድኑን ሸኝተዋል።
መቀመጫውን በደብረዘይት በማድረግ ልምምዱን ሲያከናውን የቆየዉ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በነገው ዕለት ወደ ኬንያ እንደሚያቀናም ይጠበቃል፡፡

አስተያየት ይስጡ