መቐለ 70 እንደርታ እና ፋሲል ተጋጣሚዎቻቸውን አወቁ !

 

ዛሬ ከሰዓት ካፍ ባደረገው የዙም ስብሰባ በመጪው የውድድር ዓመት በአፍሪካ የክለብ ውድድሮች ላይ የሚሳየተፉ ክለቦች የቅድመ ማጣሪያ ድልድል ይፋ አድርገዋል ።

ይህንንም ተከትሎ በአፍሪካ ሻምፒየንስ ሊግ ኢትዮጵያን የሚወክለው መቐለ 70 እንደርታ ከ ሊቢያው አህሊ ቤንጋዚያ ጋር መደልደሉን ለማወቅ ተችሏል ።

መቐለ 70 እንደርታ የመጀመሪያ ጨዋታውን ከሜዳው ውጪ የሚያደርግ ይሆናል ።

የዚህ መርሀ ግብር አሸናፊ በቀጣዪ ዙር የቱኒዚያውን ኤስፔራንስ እንደሚገጥሙ የወጣው መርሐ ግብር ያሳያል ።

በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የሚሳተፈው ፋሲል ከነማ የቱኒዚያውን ሞንስተርን ከሜዳው ውጪ ሲገጥም የዚህ መርሀ ግብር አሸናፊ የሊቢያውን አህሊ ትሪፖሊ ጋር የሚጫወት ይሆናል ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor