የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን(ካፍ) የ2025 የሴቶች አፍሪካ ዋንጫ ዳኞችን ለመምረጥ ላዘጋጀው የቅደመ ዝግጅት ስልጠና ለ59 ዳኞች ጥሪ አድርጓል።
ጥሪ ከተደረገላቸው ዳኞች መካከል 24 ዋና ዳኞች ሲሆኑ ከነዚህም መካከል ኢትዮጵያዊቷ ዋና ዳኛ ማርታ መለሰ ተካታለች።
ዋና ዳኛ ማርታ መለሰ በኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ላይ በርካታ ጨዋታዎች በጥሩ ብቃት በመምራት ብቃቷን አስመስክራለች።
ዋና ዳኛ ማርታ መለሰ የሴቶች የ17 አመት በታች የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች እንዲሁም የሴቶች ቻምፒየንስ ሊግ የሴካፋ ማጣሪያ የደረጃ ጨዋታዎችን ጨምሮ ሌሎች አህጉራዊ ጨዋታዎችን መርታለች።
- ማሰታውቂያ -
በቅርቡም በሴቶች የ17 ዓመት በታች የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ቦትስዋና ከአልጄሪያ ያደረጉትን ጨዋታ በብቃት መምራት ችላለች።
ካፍ ያዘጋጃው ይህ የቅደመ ዝግጅት ስልጠና በግብፅ ዋና ከተማ ካይሮ ከግንቦት 17 እስከ ግንቦት 22 ድረስ የሚሰጥ ይሆናል።



