ኢትዮጵያዊያን አራት አለም አቀፍ ዳኞች የካፍ ቻምፒየንስ ሊግ የሁለተኛ ዙር ጨዋታን ሊመሩ ወደ ጋቦሮኒ ያመራሉ።

የካፍ ቻምፒየንስ ሊግ የ2026/27 የማጣሪያ ጨዋታዎች የሁለተው ዙር መርሀግብር ከቀጣዩ የጥቅምት ወር የመጀመሪያ ቀናቶች ጀምሮ መካሄዳቸውን ይጀምራሉ። ከሚደረጉ ጨዋታ መካከል ጥቅምት 7/2019 ቅዳሜ አመሻሽ 12 ሰዓት ሲል ናሚቢያን ወክሎ በመድረኩ እየተካፈለ የሚገኘው እና በመጀመሪያው ዙር ማጣሪያ የጋቦኑን ኤኤስ ማንጋስፖርትን በድምር ውጤት የረታው አፍሪካን ስታርስ ቦትስዋና ጋቦሮኒ ስታዲየም ላይ የሞሪሺየሱን ክለብ ላኩር ሲልቨርስተር በመርታት ካለፈው የደቡብ አፍሪካው ጠንካራ ክለብ ኦርላንዶ ፓይረትስ ጋር የሚያደርገውን ጨዋታ አራት ኢትዮጵያን ኢንተርናሽናል ዳኞች እንዲመሩ በካፍ መመረጣቸውን ሀትሪክ ስፖርት የደረሰው መረጃ ይጠቁማል።
ጨዋታውን በመሐል ዳኝነት ቴዎድሮስ ምትኩ ሲመራው ፣ ትግል ግዛው እና ኤልያስ መኮንን በረዳት ዳኝነት እንዲሁም ሔኖክ አበበ በአራተኛ ዳኝነት በጣምራ ይመራሉ። ቦትስዋናዊ ዜግነት ያለው ሸጎፋትሶ ስታር በጨዋታ ታዛቢነት በካፍ ተመድበዋል።
አስተያየት ይስጡ