በአሜሪካ የሚገኘው ጎልደን ቡት አካዳሚ ከኦሜጋ የትጥቅ አምራች ተቋም ጋር ስምምነት ፈፀሙ።

አሜሪካን ሀገር ጎልደን ቡት የሚባል አካዳሚ በመክፈት በትልቅ ደረጃ ሲያሰለጥን የምናውቀው እና የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግን ጨምሮ በተለያዩ የአውሮፓ እና ሌሎች ሀገራትን የሚገኙ እውቅ ተጫዋቾችን የግል አሰልጣኝ በመሆን ጭምር የሚያሰለጥነው ወጣቱ አሰልጣኝ ንጉስ ሠለሞን በሀዋሳ ከተማ የእግር ኳስ ማሰልጠኛ አካዳሚን 30 ታዳጊ ተጫዋቾችን በመያዝ በይፋ የከፈተ ሲሆን ለዚህ ማሰልጠኛ እና በየአመቱ ለዕረፍት ሲመጣ ለሚያዘጋጀው የጎልደን ቡት አካዳሚ የእግር ኳስ ውድድር ከኦሜጋ ትጥቅ አምራች ተቋም ጋር በጋራ ለመስራት የትጥቅ አቅርቦት እና ሌሎች ጉዳዮች የተካተቱበት ስምምነት በዛሬው ዕለት ፈፅመዋል።

የኦሜጋ ትጥቅ አምራች ተቋም ባለቤት አቶ ፍፁም ብዙነህ ትልቅ አላማን በመያዝ የኢትዮጵያን እግር ኳስ ለማሳደግ ከሚለፉ ሰዎች ጋር በጋራ መስራታቸው እንዳስደሰታቸው ጠቅሰው በቀጣይም እንዲህ አይነት አለማን በመያዝ መስራትን እንደሚሹ ጠቁመዋል። የጎልደን ቡት አካዳሚ ባለቤት እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአካል ብቃት እና የቴክኒክ አሰልጣኝ ሆኖ የሰራው ንጉስ ሠለሞን በበኩሉ ይህ ጅምር መሆኑን በመጥቀስ በቀጣይ በትልቅ ደረጃ ራሱን የቻለ መኖሪያ ቤት ፣ መመገቢያ እና ማሰልጠኛ ያለውን ሰፊ አካዳሚ መክፈትንም እንደሚያልም ገልፆ በመጨረሻም ሁለቱም አካል የመግባቢያ ሰነድን ተፈራርመዋል።
አስተያየት ይስጡ