አራት ኢትዮጵያውያን ሴቶች ዳኞች ለሎሳንጀለስ ኦሎምፒክ የማጣሪያ ጨዋታን እንዲመሩ ተመርጠዋል።

በ2028 በሎሳንጀለስ ኦሎምፒክ ተካፋይ ለመሆን ኢትዮጵያን ጨምሮ ሀገራት የማጣሪያ ጨዋታቸውን ማድረግ ይጀምራሉ። የፊታችን ሐሙስ መስከረም 28/2019 አመሻሽ የሞሪሺየስ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በሜዳቸው ኮትዲኦር ናሽናል ስፖርት ኮንፕሌክስ የጋና ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የሚገጥምበትን ጨዋታ አራት ኢትዮጵያዊን ሴት ኢንተርናሽናል ዳኞች በካፍ እንዲመሩ መመረጣቸውን ሀገሬ ቴሌቪዥን የደረሰው መረጃ ይጠቁማል።
በዋና ዳኝነት ሲሳይ ራያ ስትመራው በረዳት ዳኝነት ወይንሸት አበራ እና ይልፋሸዋ አየለ እንዲሁም መዳብ ወንድሙ በበኩሏ አራተኛ ዳኛ በመሆን ተመርጣለች
አስተያየት ይስጡ