መነሻ ገጽ ካፍ በሴካፋ ዞን የሴቶች ቻምፒየንስ ሊግ ተካፋዩ ንግድ ባንክ ተጋጣሚዎቹን አወቀ
ካፍዜናዎች

በሴካፋ ዞን የሴቶች ቻምፒየንስ ሊግ ተካፋዩ ንግድ ባንክ ተጋጣሚዎቹን አወቀ

አጋራ
አጋራ

በሩዋንዳ በሚደረግ የሴቶች የሴካፋ ዞን የካፍ ቻምፒየንስ ሊግ የቅድመ ማጣሪያ ተካፋዩ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተጋጣሚውን ዛሬ አውቋል።

ዘጠኝ ጊዜያት ያህል የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግን ያነሳው የአሰልጣኝ ብርሀኑ ግዛው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተጠናቀቀውም አመት የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አሸናፊ መሆኑን ተከትሎ አሁንም ኢትዮጵያን ወክሎ በካፍ ቻምፒየንስ ሊግ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ላይ ይሳተፋል። በሩዋንዳዋ ኪጋሊ ከተማ ከነሐሴ 16/2018 ጀምሮ እንደሚደረግ የሚጠበቀው ይህ ውድድር በዛሬው ዕለት የምድብ ድልድል ሲወጣ ንግድ ባንክ በምድብ አንድ ከዩጋንዳው ካዌንፔ ሙስሊም ሌዲስ እና ከጅቡቲው ኤፍ ሲ ዩጂኮ ጋር ተደልድሏል።

በምድብ አንድ ደግሞ የሩዋንዳው ራዩን ስፖርት ፣ የደቡብ ሱዳኑ ይ ጆይንት ስታርስ ፣ የዛንዚባሩ ማፉንዞ ኤስ ሲ ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ክለብ የወከለችው ኤርትራ በዴንደን ስትወከል በምድብ ሦስት ደግሞ ሴናፍ ዋቁማን የግሉ ያደረገው የታንዛኒያ ሲምባ ኪዊን ፣  የኬኒያው ኬኒያ ፓሊስ እና የብሩንዲው ቶፕ ገርል አካዳሚ ተደልድለዋል።

ለዚህ ውድድር ከሳምንት በፊት በአዳማ ከተማ ዝግጅት የጀመሩት ንግድ ባንኮች አሁንም ልምምዳቸው በካኖፒ ሆቴል በማድረግ እንደቀጠሉ መሆናቸው ሀትሪክ ስፖርት አረጋግጧል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...