የአጥቂ ስፍራ ተጫዋች በድጋሚ ወደ ፈረሰኞቹ ቤት አምርቷል።
በአሁኑ ሰዓት የህክምና ምርመራውን ለማድረግ እየተጠባበቀ የሚገኘው አማኑኤል ኤርቦ በድጋሚ ፈረሰኞቹን መቀላቀል ችሏል። ከአርባምንጭ ከተማ ከተገኘ በኋላ ፣ በለገጣፎ ለገዳዲ ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና የተጠናቀቀው አመት ደግሞ በኢትዮጵያ መድን ያሳለፈው ወጣቱ አጥቂ ከአንድ አመት በኋላ ወደ ቀድሞው ክለቡ ቅዱስ ጊዮርጊስ በሁለት አመት ውል መመለሱ ተረጋግጧል።

ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ድርድር ሲያደርግ የነበረው አጥቂው በመጨረሻም ምርጫውን ፈረሰኞቹ ማድረጉም ታውቋል።
አስተያየት ይስጡ