በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ሳምንት
በተለያዩ ጥፋቶች ለተጫዋቾችና ለቡድን አመራሮች 39 ቢጫ ካርድ የተሰጣቸው ሲሆን የተመዘገበ ቀይ ካርድ የለም።
በሁለተኛው ሳምንት ውድድር የሲዳማ ቡና ክለብ የኮቪድ የምርመራ ውጤት ተዓማኒነትን ለማረጋገጥ እንዲቻል ሁሉም ክለቦች ከሁለተኛው የውድድር ሳምንት ጀምሮ
የኮቪድ ምርመራ በአክሲዮን ማህበሩ አስተባባሪነት በአንድ የምርመራ ማዕከል ብቻ እንዲያደርጉ የተወሰነውን አቅጣጫ መጣሱንና ይህም የክለቡ ድርጊት ፍትሃዊ አሰራር እንዳይሰፍን ከማድረጉ በተጨማሪ በክለቦች መካከልና በከለቦችና በአክሲዮን ማህበሩ መካከል የነበረውን
መተማመን እንዲሸርሸር ማድረጉ በውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ታምኖበታል። በመሆኑም ክለቡ ለፈጸመው ጥፋት በኢትዮጵያ እግር ኳስ የዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት የገንዘብ እንዲቀጣ ተወስኗል።
ኢትዮጵያ ቡና ክለቡ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር በነበረው የ 2ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የክለቡ ደጋፊዎች የእለቱን ዳኛ አፀያፊ ስደብ ስለመሳደባቸው ሪፖርት ቀርቦበታል ። የክለቡ ደጋፊዎች ለፈፀሙት ጥፋት ክለቡ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት የገንዘብ ቅጣት ተቀጥቷል። ሌሎች ተጨማሪ የእርምት ወሳኔዎችም ተወስነው ለክለቦች በኮሚኒኬ ተልኳል።
በዛሬው ሌላ ውሎ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊ ክለቦች የቡድን መሪዎች በመለማመጃ ሜዳ አጠቃቀም ላይ ባሉ ችግሮች ከውድድር እና ስነስርዓት ኮሚቴ ጋር ውይይት አድርገው ቀጣይ የጋራ መፍትሄውን አስቀምጠዋል።