የኢትዮጵያ ሴቶች ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ፍሬው ኃይለ ገብርኤል በዩጋንዳ አስተናጋጅነት ከጥቅምት 20 – እስከ ጥቅምት 30/2014 ለሚካሄደው የምሥራቅና መካከለኛው አፍሪካ ሀገራት ውድድር /ሴካፋ/ እያደረገ የሚገኘውን ዝግጅት አስመልክቶ ዛሬ ረቡዕ ጥቅምት 17/2014 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 ሰዓት ጀምሮ ወሎ ሰፈር በሚገኘው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መሰብሰቢያ አዳራሽ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰተዋል።
አሠልጣኝ ፍሬው ኃይለ ገብርኤል በሰጡት መግለጫ “አሁን የምናደርገው የሴካፋ ውድድር የስድስት ሀገራት ቡድኖች የምንሳተፍበት ነው፡፡ እኛም ለእነዚህ ቡድኖች የሚሆነውን ዝግጅት በተለያየ ዓይነት ዝግጅት ስንዘጋጅ መቆየታችን መግለጽ እፈልጋለሁ”፡፡ በማለት አስተያየታቸውን የጀመሩ ሲሆን አክለውም ስድስት ልጆች ወደ ዋናው ቡድን ከአደጉ በኋላ በምትካቸው ተጫዋቾችን አምጥተን ከሩዋንዳው ጨዋታ በኋላ በ8 ቀናት ልዩነት ለሴካፋው ውድደር አዳዲስ ተጫዋቾችን ጨምሮ ጥሪ ተደርጎላቸው ልምምዳችንን ስንሰራ ቆይተናል፡፡
ለ20 ዓመት በታች ቡድን ምን ዓይነት ልጆችን ነው መጠቀም የምንችለው? ሲባል ከአፈፃፀም ብቃት ውጪ እንደ ሌላው አሰልጣኝ የፈለኩትን ተጫዋች መጠቀም አልችልም የምሰራበት ቦታ ላይ ህግ አለ ህግ ያግደኛል ወደታች መውረድ አልችልም ወደላይም እድሜ ገደብ ስላለው እድሜ ያግደኛል፡፡ ይህንን ሁሉ ተጠቅሜ ለመስራት ትንሽ አስቸጋሪ ሁኔታዎች አሉ ፡፡ በሄዱ ልጀች ደሞ የሚተኩ ልጆችን እያዘጋጀሁ ነበር ፡፡ በማለት አስረድተዋል፡፡
የዝግጀት ጊዜያቸውን በተመለከተ፣
- ማሰታውቂያ -
በመጀመሪያ ቦሌ በሚገኘው ጁፒተር ኢንተርናሽናል ሆቴል ለ5 ቀናት ቆይታ ካደረጉ በኃላ በካፍ አካዳሚ ማረፊያቸውን በማድረግ ልምምዳቸውንም እዛው ሲሰሩ እንደቆዩና በቆይታቸው በርካታ አዳዲስ ወጣት ልጆችን እየጠሩ ለመምረጥ ሙከራ ማድረጋቸውን ገልፀዋል፡፡
እንደ ማሳያም “አሁን ላይ በፊት ከነበሩት ልጆች የሚቀነሱም አሉ እግር ኳስ የአፈፃፀም ብቃት የሚጠይቅ ነው፡፡ በፊት በሩዋንዳው ጨዋታ ላይ የነበሩ ልጀች የሚወጡበት መንገድ ይኖራል፡፡ እንደገና ደግሞ ወጣት ልጆችን የምናይበት ሁኔታ ይኖራል ፡፡ ቡድኑን የምናዘጋጀው ለሴካፋ እስከሆነ ድረስ በቀጣይ አገሪቱን ወክለው የሚጫወቱ ተጫዋቾችን ከመፍጠር አንፃር ሲሆን ሴካፋ ላይ በደንብ አድርገን ተጫዋቾችን ማየት ይጠበቅብናል፡፡ እኔም ትከረት አድርጌ የምሰራው እዛ ላይ ነው፡፡ በሴካፋ ልጆች ኢንተርናሽናል ልምድ ያገኙበታል ወደ 5 የሚጠጉ ጨዋታዎችን ስለሚያደርጉ በየጨዋታ ላይ አዳዲስ ነገሮችን የምንማርበት ይሆናል ጥሩም ነገር የምንሰራበት ይሆናል ብዬ አስባለሁ፡፡
በነበረን የ12 ቀናት ቆይታ ዝግጅት አድርገናል በ12 ቀናት እንግዲህ አዲስ ቡድን ነው ያደራጀነው፡፡ እንደገና የተጨመሩ ልጆች አሉ በእነዚህም ልጆች ቡድን መስርቶ ለመጓዝ ትንሽ የሚያስቸግሩ ነገሮች አሉ፡፡ ምክንያቱም አሁን ከጨዋታ የታረፈበት ጊዜ ነው ልጀችም በክለባቸው ውስጥ አይሰሩም ፡፡ በግል ሰርቶ የሚመጣ ተጫዋች ደግሞ አሁን ላይ ውጤታማ ላይሆን ይችላል፡፡ ከውድድር ላይ ቢሆን ኖሮ ሥራ ይቀላል ዞሮ ዞሮ ሴካፋ ብዙ ወጣቶች የምናይበት እና ለሀገር ግብዓት የሚሆኑ ወጣቶችን የምንይዝበት ስለሆነ ዋና መሠረት አድርጌ የምሰራው ቡድኑ ምን ያህል ኢንተርናሽናል ውድድሮችን ያገኛል ብዬ እሰራለሁ፡፡
ስለዚህ ያለን ዝግጅት በአካል ብቃት ፣በቴክኒክ፣ በታክቲክ እና ሥነ ልቦና ላይ መሠረት ያደረገ ሲሆን እንደ አዲስ የጨመርነው ሥነ-ምግብ ላይ ሲሆን ልጆቹ ምን ዓይነት ምግቦችን መመገብ እንደሚገባቸው ከተጫዋቾች ጋር በቃል እየተወያየንበት ነበር፡፡ እንዲሁም ሪከቨሪያቸውን በምን ያህል የጊዜ ልዩነት እንደሚሆን ተጨማሪ ውይይቶችን ከመስክ ልምምዱ ውጪ በክፍል ውስጥ ትምህርት ሥንሰራ ቆይተናል፡፡ሜዳላይ ብቻ ባለው ተጨዋች ይቀየራል ብዬ ስለማላስብ እና ሳይንሱም ይህንን ስለማይፈቅድና ወጣት ቡድን በመሆኑ ንድፈ ሀሳብና የተግባር ላይ ያተኮረ ስልጠና በመስጠት ይህንን ይዘን በመጓዝ መሠረት መያዙ አስፈላጊ ይሆናል ብዬ አስባለሁ፡፡ ወደ ዋናው ቡድን የጨረሰ ተጫዋች እንዲገኝ የተሻለ ሥራ ስለሚሰራ ፡፡” በማለት የዝግጅት ጊዜያቸውን አስመልክተው አስረድተዋል፡፡
በመጨረሻም ቡድኑ ኢንተርናሽናል ልምድ በማግኘት ውጤት እንዲያመጣ እንሰራለን በማለት ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ በመስጠት መግለጫውን አጠናቀዋል፡፡
©EFF