ሳላዲን ሰኢድ እና የእጅ ጉዳቱ

 

በሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ላይ የቀይ ካርድ የተመለከተው ሳላህዲን ሰኢድ ከጨዋታው መጠናቀቅ በኃላ አላስፈላጊ ሁኔታዎች ሲፈጠሩ ተጫዋቹ እጁ ላይ ጉዳት አጋጥሞት ለመመልከት ችለናል ::

ይህንንም ተከትሎ ሳላህዲን ሰኢድ በቤተዛታ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ ሲያገኝ ጉዳት በደረሰበት እጁ ላይ ህክምና አግኝቶ በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን በስፍራው ለመመልከት ችለናል ::

የክለቡ ፕሬዝዳንት አቶ አብነት ገብረ መስቀልን ጨምሮ የክለቡ ትልልቅ ሀላፊዎች በስፍራው በመገኘት ተጫዋቹን ያለበት ሁኔታ ሲያዩ በስፍራው ከሚገኙ ደጋፊዎችም ጋርም አጠር ያለ ምክክሮሽን አድርገዋል::

አቶ አብነት በስፍራው ላሉ ደጋፊዎች ሲናገሩ ተጫዋቹን የተማታው የክለቡ ደጋፊ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ሲሆን ደጋፊዎን የማስፈታት ማንኛውንም ስራ ክለቡ እንደማይሰራ እና የፖሊስ አስራርም እንደማይፈቅድ ሲገልፅ ክለቡም የራሱን እርምጃ እንደሚወስድ አያይዘው ገልፀዋል ::

ሀትሪክ ስፖርት ከታማኝ ምንጭ ባገኘችው መረጃ መሰረት ክለቡ እሁድ በቦሌ ዳግም ልምምዱን መስራት ሲጀምር በእለተ ሰኞ ከተጫዋቾቹ ጋር ስብስባ እንደሚኖራቸው ታውቋል ::

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor