መነሻ ገጽ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ 8ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች !
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎች

ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ 8ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች !

አጋራ
አጋራ

– በሳምንቱ በድምሩ የ 26,000 ብር ቅጣት ተላለፈ

– በገንዘብ እጥረት የሚገኘው ሰበታ ከተማ በርካታ ቅጣት ተጥሎበታል

– ቀጣይ ጨዋታ ሊያልፋቸው የሚችሉ ተጫዋቾች

የ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ውድድር እና አመራር በትላንትናው ዕለት ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ ጨዋታዎችን ጨምሮ ሌሎች ከዳኞች እና ታዛቢዎች የቀረቡለትን የ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የጨዋታ ሪፖርቶች መርምሮ የተለያዩ ውሳኔዎችን ማስተላለፉን ይፋ አድርጓል ።

በስምንተኛ ሳምንት በተካሄዱ የ ቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች አስራ ሰባት ጎሎች ከመረብ ሲያርፉ ካለፈው ሳምንት በሶስተ ከፍ ብሎ ተቀምጧል ።

የፋሲል ከነማው የፊት መስመር አጥቂ ሙጂብ ቃሲም በዚህኛው ሳምንት ብቸኛው ሁለት ግቦችን ማስቆጠር የቻለው ተጫዋች ሆኗል ።

በስምንተኛው ሳምንት ጨዋታዎች ሀያ ዘጠኝ ተጫዋቾች የማስጠንቀቂያ ካርዶችን ሲመለከቱ በድምሩ 210 የቢጫ ካርዶች በሊጉ ላይ ታይተዋል። በስምንተኛው ሳምንት ጨዋታዎች የሰበታ ከተማው ያሬድ ሀሰብ በቸኛው የቀይ ካርድ የተመለከተ ተጫዋች ነው  ። ከታዩ ሀያ ዘጠኝ የማስጠንቀቂያ ካርዶች ውስጥ ሀያ አንዱ ተጫዋቾች ባሳዩት ከስፖርታዊ ጨዋነት ውጪ በመሆን ወይም በመጫወት ባሳዩት ድርጊት መሆኑን ለማወቅ ተችሏል ።

በስምንተኛው ሳምንት የሊጉ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ ቡና 9.50 ነጥብ በማምጣት የዚህ ሳምንት ስፖርታዊ ጨዋነት አሸናፊ መሆናቸው ታውቋል ።

በሳምንቱ ከተላለፉ የዲሲፕሊን ውሳኔዎች መካከል :-

1.  አቶ አንበስ መገርሳ ( የሰበታ ከተማ ቡድን መሪ ) ማከሰኞ ጥር 11 ቀን 2013 ክለቡ ከ ባህርዳር ከተማ ጋር ባደረገው የ8ኛ ሳምንት ጨዋታ ካለቀ በኋላ የዕለቱን ዳኛች አፀያፊ ስድብ መሳደባቸው ከዋና ዳኛው እና ከጨዋታ ታዛቢ ሪፖርት ቀርቦባቸዋል ። የቡድን መሪው ለፈፀሙት ጥፋት በፌዴሬሽኑ የዲሲፕሊን መመሪያ መሠረት 6 ጨዋታ እንዲታገዱ እና 5,000 ብር ቅጣት እንዲከፍሉ ወስኗል።

2 . ሰለሞን ደምሴ ( የሰበታ ከተማ ግብ ጠባቂ ) ክለቡ ከባህር ዳር ከተማ ጋር ባደረጉት የ 8ኛ ሳምንት ጨዋታ ካለቀ በኋላ የዕለቱን ዳኛች አፀያፊ ስድብ መሳደቡ ከዋና ዳኛው እና ክጨዋታ ታዛቢ ሪፖርት ቀርቦበታል። ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በፌዴሬሽኑ የዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት ሶስት ጨዋታ እንዲታገድ እና 3,000 ብር የገንዘብ ቅጣት እንዲከፍል ወስኗል።

3. የሰበታ ከተማ ተጫዋች ያሬድ ሀሰን ከባህር ዳር ከተማ ባደረጉት ጨዋታ 71ኛ ደቂቃ ላይ ዳኛን አፀያፊ ስድብ በመሳደብ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል። ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት ሶስት ጨዋታ እንዲታገድ እና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 3,000 እንዲከፍል ተወስኗል።

4. ሰበታ ከተማ ከዚህ በተጨማሪም ከ ባህርዳር ከተማ ጋር ባደረጉት ጨዋታ ፋሲል ገ/ሚካኤል ፣ መሳይ ፓውሎስ እንዲሁም ያሬድ ሀሰን የማስጠንቀቂያ ካርድ መመልከታቸውን ተከትሎ የተጨማሪ  5,000 ብር የገንዘብ መቀጮ ተላልፎባቸዋል ።

5. ባህርዳር ከተማ በተቃራኒው አምስት ተጫዋቾቹ ( ሳምሶን ጥላሁን ፣ ወሰኑ አሊ ፣ ፍቅረ ሚካኤል አለሙ ፣ በረከት ጥጋቡ እና ምንይሉ ወንድሙ ) ባዩት የቢጫ ካርድ ክለቡ የ 5,000 ብር መቀጮ እንዲከፍል ተወሰኗል ።

6. ሀድያ ሆሳዕና እንደ ባህርዳር ከተማ ሁሉ አምስት ተጫዋቾቹ ( ቴዎድሮስ በቀለ ፣ ሄኖክ አርፊጮ ፣ ዱላ ሙላቱ ፣ ሳሊፍ ፎፎና እና ደረጄ አለሙ ) የማስጠንቀቂያ ካርድ መመልከታቸውን ተከትሎ ክለቡ የ 5,000 ብር ቅጣት ተላልፎበታል ።

በሊጉ አራት የቢጫ ካርዶችን ያዩ ተጫዋቾች ሲበራከቱ በዚህ ሳምንት የፋሲል ከነማዎቹ ሱራፌል ዳኛቸው እና አምሳሉ ጥላሁን ፣ የሀድያ ሆሳዕናው ተስፋዬ አለባቸው ፣ የወላይታ ድቻው እድሪስ ሰዒድ እንዲሁም የወልቂጤ ከተማው ሀብታሙ ሸዋለም እያንዳንዳቸው አራት የማስጠንቀቂያ ካርድ የተመለከቱ ከሆነ ቀጣይ የሚመለከቱ ከሆነ አንድ ጨዋታ የሚያመልጣቸው ይሆናል ።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...