ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ 20ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ቅዳሜ ሚያዝያ 16 2013 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ግጥሚያ(ዎች) ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላልፏል ።

ከነዚህም መካከል :-
1. ዳዊት እስጢፋኖስ ክለቡ ከ ወላይታ ድቻ ጋር ባደረገው የ 20 ኛ ሳምንት እግ ርኳስ ጨዋታ ላይ በ61 ኛ ደቂቃ ላይ ሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀሙ ቀይ ካርድ አይቶ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ።

ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት አንድ ጨዋታ
እንዲታገድ ተወስኗል።

2. ምኞት ደበበ ( ሀዋሳ ከተማ ) እና ባዬ ገዛኸኝ ( ባህር ዳር ከተማ ) አምስት ጨዋታዎች ላይ የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክተዋል ። በመሆኑም ተጫዋቾቹ ለፈፀሙት ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መሰረት አንድ ጨዋታ
እንዲታገዱ እና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 /አንድ ሺ አምስት መቶ/ እንዲከፍሉ ወስኗል።

3. አቶ ኃይለማርያም ፈረደ /የፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ የቦርድ አመራር / አርብ ሚያዚያ 15/2013 ዓ.ም በፋሲል ከነማ እና በሀድያ ሆሳዕና ክለቦች መካከል በተደረገው ጨዋታ ውድድሩ አንደተጠናቀቀ ባልተፈቀደላቸዉ ቦታ በመገኘት ተገቢ ያልሆነ እና ካላቸዉም የሥራ ድርሻ ጋር
በፍፁም የማይገናኝ ተግባር ሲፈፅሙ እንደተገኙ ከፀጥታ አካላት ሪፖርት ቀረቦባቸዋል።

በዚህም መነሻነት የውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ግለሰቡ በቀጣይ የፋሲል ከነማ በሚያደርጋቸዉ ቀሪ ስድስት ጨዋታዎችን ወደ ስታድየም ገብተዉ እንዳይመለከቱ ታግደዋል ፡፡

4.የሲዳማ ቡና የቡድን መሪ ክለቡ ከድሬድዋ ከተማ ጋር ለነበረበት ጨዋታ ሚያዝያ 13 2013 በተደረገው ቅድመ ስብሰባ ላይ አለመገኘታቸው በጨዋታ ታዛቢው ሪፖርት ተደርጏል :: በዚህም የሲዳማ ክለብ በውድድርና ስነስርአት ደንብ መሰረት 1000/አንድ ሺህ/ ብር እንዲቀጣ ተወስኗል ::

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor