የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ በትላንትናው ዕለት ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ ግጥሚያዎችን ጨምሮ ሌሎች ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ሪፖርቶች ከመረመረ በኋላ የተለያዩ ውሳኔዎችን ስጥቷል።
በ አስራ ሶስተኛ ሳምንት በተካሄዱ የ ቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች አስራ ስድስት ጎሎች ከመረብ አርፈዋል ።
የ ኢትዮጵያ ቡናው አቡበከር ናስር በዚህ ሳምንት ሀትሪክ መስራት የቻለው ብቸኛው ተጫዋች መሆን ሲችል የ ቅዱስ ጊዮርጊሱ ጌታነህ ከበደ ከ አንድ በላይ ጎሎችን ( ሁለት ጎሎችን ) በማስቆጠር ሌላኛው ተጫዋች ሆኗል ።
በ አስራ ሶስተኛው ሳምንት ጨዋታዎች ሀያ ሶስት ተጫዋቾች የማስጠንቀቂያ ካርዶችን ሲመለከቱ በድምሩ 333 የቢጫ ካርዶች በሊጉ ላይ ታይተዋል። በ አስራ ሶስተኛው ሳምንት ጨዋታዎች የአዳማ ከተማው ደስታ ጊቻሞ እና የ ሲዳማ ቡናው ፈቱዲን ጀማል የቀይ ካርድ የተመለከቱ ተጫዋቾች ናቸው ።
የዲሲፕሊን ውሳኔ
- ማሰታውቂያ -
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ አርብ የካቲት 19 2013 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ የኢትዮጵያ ፕሪምየርሊግ ግጥሚያ(ዎች) ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ
1. ደስታ ጊቻሞ (አዳማ ከተማ) :- ማከሰኞ የካቲት 16 2013 ዓ ም ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ13 ኛ ሳምንት እግር ኳስ ጨዋታ ላይ በ 89ኛ ደቂቃ ላይ ዳኛን አፀያፊ ስድብ በመሳድብ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት
ቀርቦበታል ።
ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት 3 ጨዋታ እንዲታገድ እና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 3000 /ሶስት ሺህ/ እንዲከፍል ወስኗል።
2. ደሳለኝ ደባሽ (አዳማ ከተማ) :- አምስት ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል።
በመሆኑም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት አንድ ጨዋታእንዲታገድ እና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 /አንድ ሺ አምስት መቶ/ እንዲከፍል ወስኗል።
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ በልዩ ሁኔታ ከስር የተቀመጡትን ሁኔታዎች አሳስቧል ።
√ የክለብ ቦርድ አባላት ፣ የደጋፊ ማህበር አባላት፣ ወይም በ ቦርድና በደጋፊ ማህበር አባላት ስም የሚገቡ ተመልካቾች በ ጨዋታዎቹ ላይ በውድድርመሪዎች፣ በራሳቸው ክለብ ላይ እና በተጋጣሚ ክለቦች ላይ አላስፈላጊና ለፀብ የሚያነሣሣ ቃላቶችን እየሰነዘሩና አልፎ አልፎም ለፀብ ሲጋበዙተስተውለዋል።
ይህ ሁኔታ በሁለተኛው ዙር ከቁጥጥር አልፎ ከፍተኛ ችግር ሳያመጣ ወደ ስታድየም በሚገቡ የቦርድ አመራሮችና የደጋፊ ማህበርአባላት ዙሪያ ውሳኔዎችን ማስተላልፍ እና ወደ ፊት መሰል ድርጊቶች እንዳይደገሙ የመጨረሻ ማሳስቢያ ለክለቦች መስጠት አስፈልጓል።
በመሆኑም :-
1.ወደ ስታድየም መግባት የሚፈቀድላችው የክለብ ቦርድ አመራሮች በፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማህበሩ የተመዘገቡና ዝርዝራቸው ለአወዳዳሪውአካል የደርስ ብቻ ይሆናል ። ስለዚህ የቦርድ አባላትን ለማህበሩ ያላሳውቃችሁ ክለቦች ህጋዊ ማህትም ባረፈበትና ፊርማ ባለው ደብዳቤ እንድታሳውቁ
2.የደጋፊ ማህበር አባላት መግባት የሚፈቅድላችው ለክለቦች በተሰጠው የ10 ሰው ኮታ ላይ ሲካተቱ ብቻ ነው በመሆኑም በማንኛውም መልኩበደጋፊ ማህበር አባልነት ስምና በደጋፊ ማህበር ቦርድ አባልነት ስም መግባት አይፈቀድም ።
3.ክለቦች የሁኔታውን አሳሳቢነት በመረዳት ከላይ በተራ ቁ. 1 ና 2 የተጠቀሱትን መመሪያዎችን በተግባር ላይ እንድታውሉና ለ ሌሎችም የ ክለባችሁ አባላትና ደጋፊዎች መመሪያዎቹን ተግባራዊ እንዲያደርጉ ሃላፊነታችሁን እንድትወጡ እያሳስብን ወደፊት በቦርድ አባላት ወይም በደጋፊዎችምክንያት ለሚፈጠሩ ችግሮች ክለቦች ላይ የውድድር አመራርና ስነ ስርዓት ኮሚቴ ጠንካራ የማስተካከያ እርምጃዎችን እንደሚወስድ ያስታውቃል ።
ጥሪ
ለኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ የቡድን መሪ እና ለሲዳማ ቡና ክለብ የቡድን መሪና የህክምና ባለሞያ አቶ አበባው በለጠ የኢትዮጵያፕሪምየር ሊግ የባህርዳር ውድድር አመራርና ስነስርዓት ኮሚቴ ሊያነጋግራችሁ ስለሚፈልግ ቅዳሜ የካቲት 20 2013 በአዝዋ ሆቴል ከጠዋቱ በ 4:00
ሰዓት እንድትገኙ ጥሪውን ያስተላልፋል ።
በሁለተኛው ዙር የሚተገበሩ ደንቦች
1.ከእረፍት በፊት በ25ኛው ደቂቃ ላይ 1 ደቂቃ እና ከ እረፍት በኃላ በ75ኛው ደቂቃ ላይ 1 ደቂቃ የውሃ እረፍት ይኖራል ።
2.ከእረፍት በኃላ ከሚቀየር/ሩ ተጫዋች/ቾች ውጭ መጫወቻ ሜዳ ውስጥ ተቀያሪ ተጫዋቾች ማሟሟቅ አይፈቀድላቸወም ።
በዕረፍት ስዓት ተቀያሪ ተጫዋቾች ወደ መልበሻ ክፍል መግባት ይኖርባቸዋል ።