ቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ በበርካታ ችግሮች ውስጥ ሆኖ ከሰዓታት በኃላ ይጀመራል

የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከቀኑ 10:00 በቅዱስ ጊዮርጊስና በሰበታ ከተማ ጨዋታ ይጀመራል።

የማስተናገድ ሀላፊነቱን የወሰደችው ድሬዳዋ ውድድሩ ያማረ እንዲሆን የተለያያ ጥረቶችን ብታደርግም የከተማዋ ከንቲባ የተከበሩ አቶ አህመድ መሀመድ ቡህ የእንግድነት ስሜት እንዳይሰማችሁ የተሻለ ነገር ለመፍጠር እንሞክራለን በማለት ለሁሉም ክለቦች (ከሀድያ ሆሳዕና በስተቀር) የእንኳን ደህና መጣችሁ የክብር የራት ግብዣ በድሬዳዋ ራስ ሆቴል በማድረግ የድሬን የእንግዳ ተቀባይነት በተግባር ቢያሳዩም ድሬዳዋና የውድድሩ የበላይ የሆነው ሊግ ካምፓኒው ከልምምድ ሜዳ ችግር፣ ከቪድና የአየር ንብረቱ ወይም ሙቀቱ ለጨዋታ ምቹ አለመሆንን ተከትሎ ከወዲሁ በበርካታ ክለቦች ወቀሳ እየደረሰባቸው ነው።

ድሬዳዋ ህዝቡና የከተማው መስተዳደር የተሻለ ቆይታ እንዲኖረን ጥረት ሲያደርጉ ቢታይም በቂ የልምምድ ሜዳ አለመኖር ያሉትም ድንጋያማና አቧራማ መሆናቸው ለልምምድ አመቺ እንዳይሆን ከማድረጉም በላይ የጤናና የጉዳት ስጋትን ይፈጥርብናል በሚል ከወዲሁ በርካታ ክለቦች ማማረር ጀምረዋል።

ከዚህ ከልምምድ ሜዳ ውጪ የድሬዳዋ የአየር ንብረት ሙቀቱ በጣም የበረታና ከ35 ድግሪ በላይ መሆኑ ሌላው ስጋታቸው እንደሆነ የሚናገሩት ክለቦች ከሁሉም በላይ ኮቪድ ተጫዋቾችን ማጥቃቱና ዳኛ እስከማስቀየር መድረሱ ነገሮችን አሳሳቢ እንዳደረገባቸው እነዚሁ የመረጃ ምንጮች ገልፀውልናል፤ለሙያው ክብር ስንል ስም ባይጠቀስም የዛሬ የ10:00 ሠዓቱን የቅዱስ ጊዮርጊስንና የሰበታን ጨዋታ የሚመራው ዳኛ የኮቪድ ምልክት በማሳየቱ ተቀይሮ ጨዋታው ሊዲያ ታፈሰ እንድትመራው መወሰኑ ተስምቷል።
ከላይ ከተቀየረው ዳኛ ሌላም ከሀዋሳ የተመረጠ ዳኛም የኮቪድ ምልክት በማሳየቱ እሱም እንዲቀየር መደረጉን ታማኝ ምንጮች ገልፀውልናል።

የቅዱስ ጊዮርጊስ ቡድን ከሜዳ፣ከሙቀት ችግር፣ከኮቪድ ጋር የሚፈጠሩ ችግሮችን በመስጋት ከሰበታ ጋር የሚያደርገውን ጨዋታ ካጠናቀቀ በኃላ ዛሬውኑ ወደ ቢሾፍቱ ለመመለስ መወሰኑን ምንጮች ጨምረው ገልፀውልናል።

Hat-trick Weekly Sport Newspaper Founder & Managing Editor.
The First Color Sport Newspaper in the country.

Yishak belay

Hat-trick Weekly Sport Newspaper Founder & Managing Editor. The First Color Sport Newspaper in the country.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *