ኮቪድ 19 ቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግን እያመሰ ነው

ድሬዳዋ ላይ እየተካሄደ ባለው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ወላይታ ድቻ በኮቪድ 19 ክፉኛ መጠቃቱ እየተነገረ ነው።

ዛሬ ምሽት አንድ ሰአት ላይ ወሳኝ ጨዋታ ከሊጉ መሪ ፋሲል ከነማ ጋር ያለው ወላይታ ድቻ 7 ቋሚ እና 1 ተጠባባቂ ተጨዋቾቹ በኮሮና ቫይረስ መጠቃታቸው ተነግሯል። የሊጉን ዋንጫ ለመውሰድ እየተቃረቡ ያሉት ፋሲሎች በወላይታ ድቻ ይፈተናሉ ቢባልም የኮቪድ 19 የጨዋታውን የሃይል ሚዛን ወደ ፋሲል ከነማ የዞረ ይመስላል።

በድሬዳዋ የኮቪድ 19 ስርጭት እየጨመረ መምጣቱና ተጨዋቾቹ በአብዛኛው የኮቪድን ፕሮቶኮል እያከበሩ አለመሆናቸው ለስርጭቱ ትልቅ አስተዋጽዎ አድርጓል ተብሏል። ቁጥሮቹ ይለያዩ እንጂ የሊጉ ክለቦች በኮቪዱ እየተጠቁ በመሆናቸው ትልቅ ርብርብ እንደሚጠይቅ ታይቷል ሊግ ካምፓኒውም ጠንካራ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎም ይጠበቃል።

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *