በድሬዳዋ ኮቪድ 19 ዳኞችን ክፉኛ አጠቃ

በድሬዳዋ እየተካሄደ ያለው የኢትዮዽያ ፕሪሚየር ሊግ በኮቪድ 19 ክፉኛ መጠቃቱ እየተነገረ ነው።
ከወደ ድሬዳዋ በተሰማ ዜና ውድድሩን ለመምራት ከተጓዙ 26 ዳኞች መሃል በዚህ ሰዓት ዝግጁ የሆኑት 8ቱ ዳኞች ብቻ ሆነዋል።

ከታማኝ ምንጭ በተገኘ መረጃ በድሬዳዋ የጤና ቢሮ ምርመራ ከተደረገላቸው 28ቱ ዋናና ረዳት አርቢትሮች መሃል 11ረዳትና7 ዋና ዳኞች ፖዘቲቭ ሆነው በመገኘታቸው ለውድድሩ ዝግጁ የሆኑት 6ዋናና 2 ረዳት ዳኞች መሆናቸው ድንጋጤን ፈጥሯል።

የድሬዳዋ ጤና ቢሮ ውጤት ትላንት ምሽት የደርሳቸው እንደተለመደወ ውጤቱን ባለ መቀበል ዛሬ ጠዋት ወደ ሀሮማያ ዩኒቨርስቲ ሄደው የድጋሚ ምርመራ እያደረጉ መሆናቸው ታውቋል።

ምርመራው በእስቸኳይ ተደርጎ ውጤቱ ካልታወቀና ካልተስተካከለ የዛሬው የጅማ አባጅፋርና የሰበታ ከተማ የወላይታ ድቻና የሀዋሳ ከተማ ጨዋታዎች በ8ቱ ዳኞች መዳፍ ላይ የወደቀ ሆኗል።

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport