ኮቪድ 19 ፕሪሚየር ሊጉ ላይ ተጽዕኖው ቀጥሏል

ለሁለተኛ ጊዜ ዳኛ የተቀየረበትን የፕሪሚየር ሊጉን ጨዋታ
ፌዴራል አርቢትር ኢያሱ ፈንቴ እንዲመራው ተደርጓል።
በጨዋታው .ጅማ አባጅፋርና ሀዋሳ ከተማ 1 ለ 1 የተለያዩ ሲሆን በኮቪድ ምክንያት ዳኛው የተቀየረበት ሁለተኛው ጨዋታ ሆኗል።

ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሰበታ ከተማ ያደረጉትን ጨዋታ እንዲመራ ተመድቦ የነበረው አርቢትር በኮቪድ በመያዙ ኢንተርናሽናል አርቢትር ሊዲያ ታፈሰ እንድትመራው መደረጉ ይታወሳል። ድሬዳዋ ላይ ያለው የኮቪድ ስርጭትም ተጠናክሮ በመቀጠሉ ስጋቱ ተባብሷል።

ትላንት ድሬዳዋ ላይ ተመርምረው ቫይረሱ አለባችሁ የተባሉ 13 የኢትዮጵያ ቡና ተጨዋቾች መንግስት የኮቪድ ምርመራ እንዲያደርጉ እውቅና ከሰጣቸው 74 ተቋማት መሃል አንዱ በሆነውና ሀረር በሚገኘው ሃሮማያ ዩኒቨርስቲ ሲመረመሩ ሁለት ተጨዋቾች ላይ ብቻ ቫይረሱ መገኘቱም አነጋጋሪ ሆኗል። እንዴትስ ተደርጎ ነው የኮቪድ 19 ፕሮቶኮል የሚከበረው የሚል ጥያቄ ተነስቶበታል። የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የጤና ቢሮ ጥያቄ የተነሳበት የኮቪድ ምርመራ ክፍተት ዙሪያ የማጣራት ስራ እየሰራ መሆኑ ተሰምቷል።

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport