ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ 9ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

 

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴረቡዕ ጥር 19 2013 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ ግጥሚያ(ዎችን) ጨምሮ ሌሎች ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ሪፖርቶች ከመረመረ በኋላ የሚከተለውን ውጤት በማፅደቅ የተለያዩ ውሳኔዎችን ስጥቷል።

በዘጠነኛው ሳምንት በተካሄዱ የ ቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች ስምንት ጎሎች ከመረብ ሲያርፉ በዘንድሮው የውድድር ዓመት አነስተኛው ሆኖ ተመዝግባል ፡፡

የድሬደዋ ከተማው ፀጋዬ ብርሐኑ ሙኸዲን ሙሳ በዚህኛው ሳምንት ብቸኛው ሁለት ግቦችን ማስቆጠር የቻለው ተጫዋች ሆኗል ።

በዘጠነኛው ሳምንት ጨዋታዎች ሀያ አምስት ተጫዋቾች የማስጠንቀቂያ ካርዶችን ሲመለከቱ በድምሩ 235 የቢጫ ካርዶች በሊጉ ላይ ታይተዋል። በዘጠነኛው ሳምንት ጨዋታዎች የቅዱስ ጊዮርጊሱ አስቻለው ታመነ እና የሰበታ ከተማው ዳንኤል ኃይሉ በሳምንቱ የቀይ ካርድ የተመለከቱ ተጫዋች ነው ።

የዲሲፕሊን ውሳኔ

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ አርብ ጥር 21 2013 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ግጥሚያ(ዎች) ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ

1. ዳንኤል ኃይሉ (ሰበታ ከተማ) ክለቡ ከ ሲዳማ ቡና ጋር ባደረገው የ 9 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ ላይ በ80 ኛ ደቂቃ ላይ የተጋጣሚን ተጫዋች በመማታት ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ። ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 3 ጨዋታ እንዲታገድ ና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 3000 /ሶስት ሺህ/ እንዲከፍል ወስኗል።

2. አስቻለው ታመነ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ክለቡ ከ ባህርዳር ከተማ ጋር ባደረገው የ 9 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ ላይ በ84 ኛ ደቂቃ ላይ የተጋጣሚን ቡድን ግልፅ ግብ የማግባት ዕድል በማበላሸት ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ። ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ 3 ጨዋታ እንዲታገድ ና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 3000 /ሶስት ሺህ/ እንዲከፍል ወስኗል።

ከላይ ከተጠቀሱት ቅጣቶች በተጨማሪም ፦

ቅዱስ ጊዮርጊስ ክለቡ ከ ባህርዳር ከተማ ጋር ባደረገው የ 9 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቡድን ተጫዋች የሆኑት ናትናኤል ዘለቀ ፤ ጋዲሳ መብራቴ ፤ አዲስ ግደይ እንዲሁም አስቻለው ታመነ በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 65 (ሐ) መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 /አምስት ሺህ/ እንዲከፍል ወስኗል፡፡

ሱራፌል ዳኛቸው(ፋሲል ከነማ) ፤ ተስፋዬ አለባቸው(ሀዲያ ሆሳዕና) እንዲሁም እንድሪስ ሰይድ(ወላይታ ድቻ) በ አምስት ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ የተመለከቱ በመሆኑ ተጫዋቾቹ ለፈፀሙት ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 5 አንቀፅ 35 በተቁ 1 (መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ ና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 /አንድ ሺ አምስት መቶ/ እንዲከፍ ወስኗል።

በሊጉ አራት የቢጫ ካርዶችን ያዩ ተጫዋቾች ሲበራከቱ የፋሲል ከነማው አምሳሉ ጥላሁን ፣ የባህርዳር ከተማው ፍቅረሚካኤል አለሙ እንዲሁም የወልቂጤ ከተማው ሀብታሙ ሸዋለም እያንዳንዳቸው አራት የማስጠንቀቂያ ካርድ የተመለከቱ ከሆነ ቀጣይ የሚመለከቱ ከሆነ አንድ ጨዋታ የሚያመልጣቸው ይሆናል ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor