መነሻ ገጽ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 23ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግዲሲፕሊን ውሳኔ

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 23ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

አጋራ
አጋራ

በ23ተኛ ሳምንት የተደረጉ ጨዋታዎችን መሰረት በማድረግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዉድድር አመራር እና ስነስርዓት ኮሚቴ የዲሲፕሊን ዉሳኔዎችን ይፋ አድርጓል።

* በተጫዋቾች ደረጃ :- ያሬድ ባየህ እና ፍፁም አለሙ በቀይ ካርድ ከሜዳ በመሰናበታቸዉ ምክንያት 1 ጨዋታ ሲታገዱ ደጉ ደበበ፣ ያሬድ ዳዊት ፣ኡመድ ኦክዋሪ ፣ አቤል አሰበ ፣ ሙና በቀለ እና ይሁን እንዳሻው በተለያዩ ጨዋታዎች 5 የቢጫ ካርድ የተመለከቱ ስለሆነ በቀጣይ የ24ኛዉ ሳምንት ጨዋታ የሚያልፋቸዉ ሲሆን በተጨማሪም 1500 ብር እንዲከፍሉ ተወስኗል።

* በክለቦች ደረጃ :- ፋሲል ከነማ እና ባህርዳር ከተማ በነበራቸዉ ጨዋታ ተጫዋቾቻቸው 5 ቢጫ ስለተመለከቱ በመመሪያዉ መሰረት 5000 ብር እንዲከፍሉ ሲወሰን በተጨማሪም የባህርዳር ከተማ ደጋፊዎች በእለቱ ጨዋታ የውድድር አመራሮችን ፀያፊ ስድብ ስለመሳደባቸው ምክንያት 50,000 ብር እንዲከፍል ውሳኔ ተላልፏል።

* በቡድን አመራሮች ደረጃ ደግሞ አቶ አሸብር አሰፋ (ሲዳማ ቡና የቡድን መሪ) ክለባቸው ከፋሲል ከነማ ጋር በነበረው የ22ኛ ሳምንት ቅድመ ጨዋታ ስብሰባ ወቅትና የዕለቱ ጨዋታ ከተጠናቀቀ በኋላ ፀብን የሚያነሳሳ ንግግር ስለመናገራቸው እንዲሁም ውድድሩ ከተጠናቀቀ በኋላ በእለቱ ዋና ዳኛ ላይ በሃሰት የተመሰረተ ትችት ስለመስጠታቸው ሪፖርት የቀረበባቸው በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 3 ወር እንዲታገዱና ብር 10,000 ብር እንዲከፍሉ ተወስኗል።

ከዚህ በተጨማሪም አቶ አዳሙ ኑመሮ (ሃዋሳ ከተማ) የግብ ጠባቂ አሰልጣኝ) ክለባቸው አዲስ አበባ ከተማ ጋር በነበረው የ23ኛ ሳምንት እግር ኳስ ጨዋታ ዳኛን አፀያፊ ስደብ ተሳድበው በቀይ ካርድ ከሜዳ ስለመወገዳቸው ሪፖርት የቀረበባቸው አሰልጣኙ ባጠፉት መሰረት 3 ጨዋታ እንዲታገዱና 10,000 ብር እንዲከፍሉ ተወስኗል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...

ዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

አንጋፋው አሰልጣኝ በስማቸው የእግር ኳስ ማሰልጠኛ አካዳሚ ሊገነባላቸው ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ አሰልጣኝ ኢንስትራክተር ሰውነት ቢሻውን ለማመስገን እና ዕውቅና ለመስጠት...