👉 ሶስት የታገዱና ቅጣቱ የተነሳላቸው ዳኞች
ተካተዋል….
👉 የአበል ክፍያም ለዳኞቹ መክፈል አልተቻለም
ተብሏል….
ወደ ወሳኝ ምዕራፍ እየተሻገረ ያለው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከነገ በስቲያ ቅዳሜ በባህርዳር ኢንተርናሽናል ስታዲየም ሲቀጥል ጨዋታውን የሚመሩት 24 ዳኞች ባህርዳር ከተማ ገብተዋል።
ከ1-21ኛ ሳምንት ድረስ የተካሄደው የአመቱ መርሃግብር በሀዋሳ ከተማ፣ ድሬዳዋ ከተማና አዳማ ከተማ ከተካሄደ በኋላ ከ22ኛ ሳምንት እስከ 30ኛ ድረስ ያለው በባህርዳር ከተማ በቀን ሶስቴ በሚካሄድ ውድድር ይቀጥላል።
ይህን ጨዋታ ለመምራት በብሄራዊ ዳኞች ኮሚቴ የተመረጡት አብዛኞቹ ዳኞች ባህርዳር ከተማ የገቡ ሲሆን አስገራሚ የሚሆነው አወዳዳሪው አካል የሆነው የፕሪሚየር ሊጉ የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ የተመደቡትን ዳኞች ዝርዝር እስካሁን አለማወቁና የአበል ክፍያ መፈጸም አለመቻሉ ነው።
የብሄራዊ ዳኞች ኮሚቴ የመረጣቸውን ዳኞች ዝርዝር አለመላኩ ሊግ ኩባንያው ምንም ማድረግ የማይችል ጥርስ የሌለው አንበሳ አድርጎ መቁጠሩን ያሳያል ለዳኞቹ የሙያና የአበል ክፍያ የሚከፍለው ሊግ ኩባንያው ቢሆንም በፌዴሬሽኑ ጡጫ የተማመነው ብሄራዊ ዳኞች ኮሚቴ የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴው አቅም የሌለው መሆኑን ያመነ ይመስላል። የዳኞቹ ዝርዝር ባለመላኩም ለዳኞቹ እንደቀድሞው አበላቸውን በጊዜ መክፈል አለመቻሉም ታውቋል።
ሊግ ኩባንያው ከ21-23ኛ ሳምንት ላለው 24 ግጥሚያዎች የተመደቡትን 12 ዋናና 12 ረዳት ዳኞች ከመቀበል ውጪ ቅሬታ ማንሳት እንደማይችል ብሄራዊ ዳኞች ኮሚቴ ማመኑን የሊግ ኩባንያውና 16ቱ ክለቦች ድምጽ የመታፈኑን ነገር የሚያሳይ ሆኗል።
ከውስጥ አዋቂ በተኘገኘ መረጃ መሠረት ኢንተርናሽናል አርቢትር ለሚ ንጉሴና ኢንተርናሽናል አርቢትር አሸብር ሰቦቃ ውጪ ሌሎቹ ፌዴራሎች ሲሆኑ እነሱም ፌዴ.አርቢትር ኢያሱ ፈንቴ ፣ ፌዴ.አርቢትር ኤፍሬም ደበሌ፣ ፌዴ.አርቢትር ባህሩ ተካ፣ ፌዴ.አርቢትር ዮናስ ማርቆስ፣ ፌዴ.አርቢትር ዮናስ ካሳሁን፣ ፌዴ.አርቢትር ሚካኤል ጣዕመ፣ ፌዴ.አርቢትር ተከተል ተሾመ፣ ፌዴ.አርቢትር ተስፋዬ ጉርሙ እንዲሁም ታግደው ቅጣቱ የተነሳላቸው ፌዴ.አርቢትር ምስጋናው መላኩ፣ ፌዴ.አርቢትር አለማየሁ ለገሠ መሆናቸው ታውቋል።
12 ረዳት ዳኞች ደግሞ ፌዴ.ረዳት ዳኛ አሸብር ታፈሰ፣ ፌዴ.ረዳት ዳኛ ሰለሞን ተስፋዬ፣ ፌዴ.ረዳት ዳኛ ካሳሁን ፍፁም፣ ፌዴ.ረዳት ዳኛ ኤፍሬም ሃ/ማርያም፣ ፌዴ.ረዳት ዳኛ አብዱ ይጥና፣ ፌዴ.ረዳት ዳኛ ተከተል በቀለ፣ፌዴ.ረዳት ዳኛ ድሪባ ቀነኒሳ፣ፌዴ.ረዳት ዳኛ ሸዋንግዛው ይልማ፣ፌዴ.ረዳት ዳኛ አያሌው አሰፋ፣
ፌዴ.ረዳት ዳኛ ማንደፍሮ አበበና ፌዴ.ረዳት ዳኛ
ፍረዝጊ ተስፋዬ ሲሆኑ በዚህ ስብስብ ውስጥ ከተቀጣ ሶስት ወር ያልሞላው ኢንተርናሽናል አርቢትር ክንዴ ሙሴም መካተቱ ታውቋል።
በ22ኛው ሳምንት መርሃግብር መሰረት ጅማ አባጅፋር ከአርባምንጭ፣ ኢትዮጵያ ቡና ከድሬዳዋ ከተማ፣ ሀድያ ሆሳዕና ከመከላከያ፣ ሰበታ ከተማ ከሀዋሳ ከተማ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአዳማ ከተማ፣ወላይታ ድቻ ከባህርዳር ከተማ ፣ ሲዳማ ቡና ከፋሲል ከነማ እንዲሁም ወልቂጤ ከተማ ከአዲስ አበባ ከተማ ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።
አስተያየት ይስጡ