በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በ21 ነጥብ 14ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው አዲስ አበባ ከተማ ለቀጣዮቹ ዘጠኝ ጨዋታዎች አሰልጣኝ ጳውሎስ ጌታቸውን ሾሟል።
ከታማኝ ምንጭ በተገኘ መረጃ አሰልጣኙ ኢዮብ ማለ
/አሞካቺን / ምክትሉ በማድረግ ወደ ባህርዳር አቅንተዋል። ቀጣይ ዘጠኝ ጨዋታ ተሳክቶ አዲስ አበባ ከተማ ከመውረድ ከተረፈ ውሉን በቋሚነት ለማድረግ የክለቡ አመራሮችና አሰልጣኙ ተስማምተዋል።
አዲስ አበባ ከተማ በቀድሞ አሰልጣኞቹ ደምሰው ፍቃዱና አሳምነው ገ/ወልድ ስር ባደረጋቸው 21 ጨዋታዎች 21 ነጥብና 2 የግብ ዕዳ ይዞ 14ኛ ደረጃ ላይ መገኘቱ አመራሮቹ እንዲያሰናብቷቸው ያደረገ ሲሆን አሰልጣኝ ጳውሎስ የመጀመሪያ ጨዋታውን የፊታችን ሰኞ 10 ሰአት ቀድሞ ካሰናበተው ከወልቂጤ ከተማ ጋር የሚጫወት መሆኑ ግጥምጥሞሹን ልዩ አድርጎታል።
አስተያየት ይስጡ