መነሻ ገጽ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተጠባቂው የ30ኛ ሳምንት ቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ የውድድር መርሃ ግብር ይፋ ሆኗል
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ተጠባቂው የ30ኛ ሳምንት ቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ የውድድር መርሃ ግብር ይፋ ሆኗል

አጋራ
አጋራ

ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2014 ዓ.ም የሻምፒዮና ትንቅንቁም ሆነ የመውረድ ጉዳይ ሳይለይ አጓጊ በሆነ መንገድ 30ኛ ሳምንት ላይ መድረሱ ይታወቃል። ቀደም ብሎ እንደተገለፀው የ30ኛ ሳምንት ውጤት ተስተካክሎ ይፋ ተደርጓል። የሊጉ ውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ የውድድር ደንብ አካሄዶችን ታሳቢ በማድረግ ተከታታይ ውይይት ካደረገ በኋላ ከታች ያለውን ፕሮግራም ይፋ አድርጎ ዛሬ ሰኔ 22/2014 ዓ.ም ለክለብ ቡድን መሪዎች በተዘጋጀ መድረክ አሳውቋል።

በዚህ መሰረት አርብ ሰኔ 24/2014 ዓ.ም በተመሳሳይ ሰዓት ሶስት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ። የአርብ መርሃ ግብር በባህርዳር አለም አቀፍ ስታዲየም ያለ ጨዋታ በሱፐርስፖርት ቀጥታ ስርጭት፣ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ያለ ጨዋታ በአማራ ሚድያ ኮርፖሬሽን ቀጥታ ስርጭት ሲኖረው በአጼ ቴዎድሮስ የሚካሄደው ጨዋታ በሱፐር ስፖርት ቀረፃ ይደረግበታል። የዋንጫ መርሃ ግብር በእለቱ አርብ ሰኔ 24/2014 ዓ.ም በባህር ዳር አለም አቀፍ ስታዲየም በሚዘጋጅ መድረክ የሚካሄድ ይሆናል።

ሐሙስ ሰኔ 23 2014
04:00 ወላይታ ድቻ – ወልቂጤ ከተማ – ባህር ዳር አለም አቀፍ ስታዲየም
07:00 ሰበታ ከተማ – አርባምንጭ ከተማ – ባህር ዳር አለም አቀፍ ስታዲየም

አርብ ሰኔ 24 2014
04:00 ሃዋሳ ከተማ – አዳማ ከተማ – አፄ ቴዎድሮስ ስታዲየም
04:00 ድሬደዋ ከተማ – ፋሲል ከነማ – ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም
04:00 ቅዱስ ጊዮርጊስ – አዲስ አበባ ከተማ – ባህር ዳር አለም አቀፍ ስታዲየም

ቅዳሜ ሰኔ 25 2014
04:00 ጅማ አባ ጅፋር – መከላከያ – ባህር ዳር አለም አቀፍ ስታዲየም
07:00 ሲዳማ ቡና – ሀዲያ ሆሳዕና – ባህር ዳር አለም አቀፍ ስታዲየም
10:00 ኢትዮጵያ ቡና – ባህርዳር ከተማ – ባህር ዳር አለም አቀፍ ስታዲየም

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...