በኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ እየተመሩ በዝዉዉር መስኮቱ በርካታ የሚባሉ ተጫዋቾችን በማስፈረም ላይ የሚገኙት ባህርዳር ከተማዎች አሁን ደግሞ ተከላካዩን ፈቱዲን ጀማልን ከሲዳማ ቡና ማስፈረም ችለዋል።
በ2011 የዉድድር አመት በሲዳማ ቡና ቤት ባሳየዉ ድንቅ ብቃት ምክንያት በቀጣዩ የዉድድር አመት የካሳየ አራጌን ኢትዮጵያ ቡና ተቀላቅሎ መጫዎቱ ይታወሳል ፤ ዉድድሩም በCOVID-19 እስከተቋረጠበት ጊዜ ድረስ ከወንድሜነህ ደረጀ ጋር በመጣመር ጥሩ አመትን ማሳለፍ ቢችልም ከክለቡ ጋር ባለመስማማቱ ምክንያት ከአንድ አመት ቆይታ በኋላ ወደ ቀድሞ ክለቡ ሲዳማ ቡና መመለሱ ይታወሳል።
የዘንድሮውን የዉድድር አመት በሲዳማ ቡና ያሳለፈዉ ተከላካዩ አሁን ደግሞ ለሁለት አመት በሚቆይ የኮንትራት ዉል ባህርዳር ከተማን ተቀላቅሏል።


