ሶስት ሰዓት ላይ ተጠባቂ የነበረው የዱራሜ ከነማ እና የዱከማ ጨዋታ በዱራሜ ከነማ ሁለት ለአንድ አሸናፊነት ተጠናቋል
በርካታ ልምድ ያላቸውን ተጫዋቾች የያዘው ዱከም ጎል ለማስቆጠረ ሰባት ደቂቃ ብቻ ነው የፈጀባቸው ።በቀኝ መስመር በኩል ክሮስ የተደረገው ኳስ በዱራሜ ከነማዎች ተጨርፋ ጎል ሆናለች ።ሙሉ በሙሉ ታዳጊ ተጫዋቾችን የያዙት ዱራሜ ከነማዎች ወደ ጨዋታ ለመመለስ ብዙም ደቂቃ አልፈጀባቸውም በስምንት ደቂቃ ልዩነት ጎል አስቆጥረዋል ።ከቅጣት ምት ክሮስ የተደረገውን ኳስ ባፋ ወደ ጎል መክሮት የዱከም በረኛ ያዘው ሲባል ከእጁ ስር ሾልካ አጠገቡ የነበረው ሀይሌ አለሙ ወደ ጎልነት ቀይሯት የመጀመሪያው አጋማሽ በአንድ አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል።

ዱራሜ ከነማዎች ሁለተኛው አጋማሽ በተጀመረ በአምስት ደቂቃ ውስጥ ጎል አስቆጥረዋል ።ከቀኝ መስመር የተገኘውን ቅጣት ምት አነቦ ወደ ጎልነት ቀይሮታል ።ከጎሏ መቆጠር በኋላ ዱከሞች ጎል ለማስቆጠር በተደጋጋሚ ሙከራ ቢያደርጉም የዱራሜ ከነማዎችን የተከላካይ መስመር ጥሰው መግባት አልቻሉም።ዱራሜ ከነማዎችም በመልሶ ማጥቃት በርካታ ኳሶችን ቢያገኙም መጠቀም አልቻሉም ።በመጨረሻም ጨዋታው በዱራሜ ሁለት ለአንድ በሆነ ውጤት ተጠናቋል።
- ማሰታውቂያ -
ሌላኛው ተጠባቂ ጨዋታ ስምንት ሰዓት የጀመረው የሲዳማ ተወካዩ ምስራቅ ክፍለ ከተማ እና የዱብቲ ወረዳ ጨዋታ በምስራቅ ክ/ከተማ ሶስት ለባዶ አሸናፊነት ተጠናቋል።
በርካታ ወጣት ተጫዋቾችን የያዘው ምስራቅ ክ/ከተማ ገና ጨዋታው ከመጀመሩ አንስቶ ነው የዱብቲ ወረዳን ጎል መፈተሽ የጀመሩት። ተደጋጋሚ ሙከራዎችን በቢንያም ባንጫ እና በታምራት ዋና ማድረግ ቢችሉም ጎል ግን ማስቆጠረ አልቻሉም ።ከብዙ ሙከራ በኋላ በጨዋታው ድንቅ እንቅስቃሴ ሲያደርግ ከነበረው ቢንያም ባንጫ አሲስት የተደረገለትን ኳስ ታምራት ዋና በግሩም ሁኔታ አስቆጥሯል።
ከጎሏ በኋላ ዱብቲ ወረዳዎች በመልሶ ማጥቃት ሙከራዎችን ለማድረግ ጥረት ቢያደርጉም ጎል ግን ማስቆጠር አልቻሉም ። የመጀመሪያው አጋማሽም በምስራቅ ክ/ከተማ አንድ ለባዶ መሪነት ተጠናቋል።

ሁለተኛው አጋማሽ ላይ ተጨማሪ አጥቂዎችን ቀይረው የገቡት ምስራቅ ክ/ከተማዎች ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ የጨዋታ ብልጫን ወስደዋል ።በተደጋጋሚ ሙከራ ሲያደርጉ ውለው በመጨረሻ ጎል አስቆጥረዋል ።ቢንያም ባንጫ ላይ የተሰራውን ጥፋት ተከትሎ የተኘውን ቅጣት ምት ራሱ ቢንያም ባንጭ በግሩም ሁኔታ ከርቀት አስቆጥሯል።ከጎሏ መቆጠረ በኋላ ተጭነው መጫወታቸውን የቀጠሉት ምስራቅ ክ/ከተማዎች ተቀይሮ በገባው በረከት ገዛኸኝ አማካኝነት ሶስተኛ ጎል አስቆጥረው ጨዋታው በምስራቅ ክ/ከተማ ሶስት ለባዶ አሸናፊነት ተጠናቋል።
አስር ሰዓት ላይ በሀረር ሸንኮር ወረዳ እና በጋምቤላው አብይ አካዳሚ የተደረገው ጨዋታ በአብይ አካዳሚ ሶስት ለዜሮ አሸናፊነት ተጠናቋል ።
ከ20 ዓመት በታች ወጣቶችን ብቻ ይዞ የቀረበው ሸንኮር ወረዳ በመጨረሻም ለአብይ አካዳሚ እጁን ሰቷል ።አብዛኛውን የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ኳስን በመሬት በማንሸራሸር እና በአንድ ሁለት ቅብብል ማራኪ ጨዋታን አሳይተዋል ።አብይ አካዳሚዎች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ረጃጅም ኳሶችን በመጠቀም ጎል ለማስቆጠር ጥረት ቢያደርጉም ጎል ለማስቆጠር ረጅም ደቂቃ መጠበቅ ግድ ሆኖባቸዋል ።
ሸንኮር ወረዳዎችም በመልሶ ማጥቃት ተደጋጋሚ ኳሶችን ቢያገኙም ከልምድ ማጣት አንፃር ወደ ጎል መቀየር አልቻሉም ።
ከእረፍት መልስ ይበልጥ እያማረ የመጣው የሁለቱም ጨዋታ በርካታ ሙከራዎች ተደርገውበታል ።ሸንኮር ወረዳዎች በተደጋጋሚ ሶስት ለአንድ ቢገናኙም አሁንም በልምድ ችግር ጎል ማስቆጠር አልቻሉም

ሰዓቱ በሄደ ቁጥር ይበልጥ ረጃጅም ኳሶች በተደጋጋሚ ወደ ጎል ሲጥሉ የነበሩት አብይ አካዳሚዎች በመጨረሻም ጥረታቸው ፍሬ አፍርቶ በ83ኛው ከቀኝ መስመር ክሮስ የተደረገው ኳስ ተጨራርፋ በቀላሉ ጎል አስቆጥሯል: በዚህ ያላበቁት አብይ አካዳሚዎች በኮርግንግ ቦል ሁለተኛ ግሩም ጎል አስቆጥረዋል ።በመጨረሻም ኮርግንግ ቦል ሀትሪክ የሰራበትን ሶስተኛ ጎል አስቆጥሮ አብይ አካዳሚዎች ሶስት ለባዶ አሸንፈዋል።
* ስለ ሀረር ሸንኮር ወረዳ እግር ኳስ ክለብ ሰፋ ያለ ዘገባ ይዘን እንመለሳለን ።
የኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና ሁለተኛ ቀን ውሎ ውጤቶች
ምስራቅ ክፍለ ከተማ 3-0 ዱብቲ ወረዳ
ሀዋሳ አርቴፊሻል ስታድየም
አብይ አካዳሚ 3-0 ሸንኮር ወረዳ
ሀዋሳ አርቴፊሻል ስታድየም
ቦዲቲ ከተማ 1-0 ጉንዶ መስቀል
ሀዋሳ ደቡብ ኮሌጅ ሜዳ
ኩምሩክ ከተማ 1-2 ኢታንግ ከተማ
ሀዋሳ ደቡብ ኮሌጅ ሜዳ
ጋምቤላ ዩንቨርስቲ 0-3 ዋግ ኽምራ
ሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ሜዳ
መንጌ ቤንሻንጉል 0-2 ምህረት
ሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ሜዳ
ካራማራ ክለብ 1-0 ሐረር ፖሊስ
ሀዋሳ አርቴፊሻል ስታድየም
ዱብቲ ከተማ 0-1 ወረኢሉ ለገሂዳ
ሀዋሳ አርቴፊሻል ስታዲየም
ዱከም ከተማ 1-2 ዱራሜ ከተማ
ሀዋሳ ደቡብ ኮሌጅ ሜዳ
ቤጉ ፖሊስ 1-0 አለታ ጪኮ
ሀዋሳ ደቡብ ኮሌጅ
ካማሺ ከተማ 3-0 ዋልያ ድሬ
ሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ስታድየም
ሀሁ አዲስ ከተማ 1-2 ሊሙ ገነት
ሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም


