መነሻ ገጽ ዜናዎች ኢትዮ-አፍሪካ የአሰግድ ተስፋዬ የመታሰቢያ ውድድር ሻምፒዮና ሆነ
ዜናዎች

ኢትዮ-አፍሪካ የአሰግድ ተስፋዬ የመታሰቢያ ውድድር ሻምፒዮና ሆነ

አጋራ
አጋራ

እውቁን የቀድሞ የሀገር ባለውለተኛና ድንቅ የአጥቂ ስፍራ ተጨዋችን አሰግድ ተስፋዬን/ጂሪየስ/ የአራተኛ ዓመት ህልፈትን አስመልክቶ በ8 ክለቦች መካከል ሲካሄድ የቆየው የመታሰቢያ እግር ኳስ ውድድር በዛሬው ዕለት ፍፃሜውን ያደረገ ሲሆን በዕለቱም በተደረገው ጨዋታ የኢትዮ-አፍሪካንና የአበበ ቢቂላ የጤና ቡድኖች በመደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ምርጥ የጨዋታ ፉክክርን ካደረጉ በኋላ ለኢትዮ-አፍሪካ አብዱራህማን መሀመድ /አቡሸት/

ለአበበ ቢቂላ ደግሞ ዳዊት ባሌማ ባስቆጠሯቸው ግቦች 1-1 ከተለያዩ በኋላ የሁለቱን ቡድኖች አሸናፊ ለመለየት በተሰጡት የፍፁም ቅጣት ምቶች ኢትዮ-አፍሪካ 5-4 በአጠቃላይ የጨዋታ ውጤት ደግሞ 6-5 በማሸነፍ የውድድሩ ሻምፒዮና ሆነዋል።

ኢትዮ-አፍሪካ ይህን ውድድር ለመጀመሪያ ጊዜ ሻምፒዮና የሆነበት ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ የተደረገውን ውድድር ደግሞ የሻላ የጤና ቡድን ማሸነፉ ይታወሳል።
በኢትዮ-አፍሪካና በአበበ ቢቂላ የጤና ቡድኖች መካከል ዛሬ በተደረገው ጨዋታ 95ኛው ደቂቃ ላይ የአበበ ቢቂላው ግብ ጠባቂ ሄኖክ /ቤንዜማ/ ከኢትዮ-አፍሪካው አጥቂ አብዱራህማን ሙባረክ /ግሪዳው/ ጋር በመጋጨቱ ጠንከር ያለ የእግር ላይ ጉዳትን ያስተናገደ ሲሆን የመጀመሪያ ህክምናውንም በሜዳ ላይ ካስተናገደ በኋላም ወደ ሳሮን ሆስፒታል ተወስዶ ሄክምናውን እያደረገ ይገኛል።

የአሰግድ ተስፋዬ የመታሰቢያ እግር ኳስ ውድድር በዛሬው ዕለት ሲጠናቀቅም የኢትዮ-አፍሪካውያኖቹ ቢኒያም ሀይሌ በኮከብ ተጨዋችነት፣ ሚራጅ በኮከብ ግብ አግቢነት፣ ውብሸት ደሳለኝ በኮከብ ግብ ጠባቂነትና ሳሙሄል በኮከብ አሰልጣኝነት በመመረጥ ተሸላሚ ሆነዋል። የውድድሩን የስፖርታዊ ጨዋነት ሽልማት ደግሞ የኮተቤ የጤና ቡድን ሲወስድ ከዋንጫው በፊት በተደረገው የውድድሩ ማድመቂያ ጨዋታ ደግሞ በአሰልጣኝ ታምሩ ከበደ የሚመራው የዲጂዎች ቡድን የስፖርት ጋዜጠኞችን ቡድን 3-0 በማሸነፍ ዋንጫ ሊሸለሙ ችለዋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...