በ2013 የዉድድር አመት ከከፍተኛ ሊጉ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ከተመለሱ በኋላ በዘንድሮዉ የዉድድር አመት በሊጉ ጠንካራ ተፎካካሪ ሆነዉ 40 ነጥቦችን በመሰብሰብ 7ኛ ደረጃን ይዘዉ ማጠናቀቅ የቻሉት አርባምንጭ ከተማዎች የአሰልጣኛቸዉን መሳይ ተፈሪ ዉል ለተጨማሪ አመት አራዝመዋል።
አዞዎቹ የአሰልጣኛቸዉን ዉል ማራዘማቸውን በተጨማሪ ደግሞ የዉድድር አመቱን በአዲስአበባ ከተማ ያሳለፈዉን የተከላካይ ስፍራ ተጫዋቹን እዮብ በቀታን በአንድ አመት ዉል ማስፈረማቸዉ ተረጋግጧል።
አስተያየት ይስጡ