👉እስካሁን ፌዴሬሽን ያወቀው ዝውውር
የአራት ክለቦችን ነው።
ሀምሌ 1 በይፋ በተከፈተው የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ባለፉት ስድስት ቀናት ብቻ ህጋዊ ዝውውር ያደረጉት ተጨዋቾች ከ20 እንደማይበልጡ ተነገረ።
ከክለቦቹ ታማኝ ምንጭ በተገኘ መረጃ ኢትዮጵያ ቡና ብሩክ በየነ፣ አብዱልከሪም ወርቁ፣ ጫላ ተሺታ፣ ሀይለሚካኤል አደፍረስ፣ አብዱል ሀፊዝ ቶፊቅና መስፍን ታፈሰን ሲያስፈርም የሮቤል ተ/ሚካኤል ውልን ማራዘሙ ታውቋል። በርካታ ዝውውር እያደረገ ነው የተባለው መከላከያ በረከት ደስ፤ ዳግም ተፈራ፣ ምንይሉ ወንድሙና ሳሙኤል ሳሊሶን ሲያስፈርም ፋሲል ከነማ በበኩሉ የበዛብህ መለዮ፣ የሱራፌል ዳኛቸውና የሽመክት ጉግሳን ውል ሲያድስ ባህርዳር ከተማ ፍጹም ጥላሁን፣ ያሬድ ባዬህና ዱሬሳ ሹቢሳን ማስፈረሙ ታውቋል።
ከ16ቱ ክለቦች እስካሁን በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ማረጋገጫ ያገኙት አራት ክለቦች ብቻ መሆናቸው ታውቋል።
አስተያየት ይስጡ