የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ በትላንትናው ዕለት ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ ግጥሚያ(ዎችን) ጨምሮ ሌሎች ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ሪፖርቶች ከመረመረ በኋላ የተለያዩ ውሳኔዎችን ስጥቷል።
በ አስራ አራተኛ ሳምንት በተካሄዱ የ ቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች አስራ ስድስት ጎሎች ከመረብ አርፈዋል ። የኢትዮጵያ ቡናው አቡበከር ናስር እና የሰበታ ከተማው ፍፁም ገብረ ማርያም ከ አንድ በላይ ጎሎችን ( ሁለት ጎሎችን ) ማስቆጠር የቻሉ ብቸኞቹ ተጫዋች ሆኗል ።
በ አስራ አራተኛው ሳምንት ጨዋታዎች ሰላሳ ሶስት ተጫዋቾች የማስጠንቀቂያ ካርዶችን ሲመለከቱ በድምሩ 366 የቢጫ ካርዶች በሊጉ ላይ ታይተዋል። በ አስራ አራተኛው ሳምንት ጨዋታዎች የ ሲዳማ ቡናው ሀብታሙ ገዛኸኝ የቀይ ካርድ የተመለከተ ብቸኛው ተጫዋቾች ናቸው ። ሲዳማ ቡና በሊጉ በተከታታይ የጨዋታ ሳምንታት ላይ ( ፈቱዲን ጀማል በ 13ኛው ሳምንት ) የቀይ ካርድን ሊመለከቱ ችሏል ።
የዲሲፕሊን ውሳኔ
- ማሰታውቂያ -
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ዕሮብ የካቲት 24 2013 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ የኢትዮጵያ ፕሪምየርሊግ ግጥሚያ(ዎች) ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ
1. ሀብታሙ ገዛኸኝ (ሲዳማ ቡና ) :- ማከሰኞ የካቲት 23 2013 ዓ ም ክለቡ ከ ባህርዳር ከተማ ጋርባደረገው የ 14 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ ላይ በ89 ኛ ደቂቃ ላይ ሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀሙ ቀይ ካርድአይቶ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ።
ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት አንድ ጨዋታ እንዲታገድ ወስኗል።
2. ወንድማገኝ ማርቆስ (ጅማ አባጅፋር) :- አምስት ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል።
በመሆኑም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት አንድ ጨዋታ እንዲታገድ እና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 /አንድ ሺ አምስት መቶ/ እንዲከፍል ወስኗል።
3. ጅማ አባጅፋር ከ አዳማ ከተማ ጋር ባደረገው ጨዋታ አብርሀም ታምራት ፣ አቡበከር ኑሪ ፣ አማኑኤል ተሾመ ፣ ሳምሶን ቆልቻ እና ወንድማገኝ ማርቆስ የቢጫ ካርድ መመልከታቸውን ተከትሎ ብር 5,000 ( አምስት ሺህ ብር ) የገንዘብ መቀጮ ተላልፎባቸዋል ።
4. በፋሲል ከነማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ከለቦች መካከል እሁድ የካቲት 21 2013 በተደረገው ጨዋታ ውድድሩ አንደተጠናቀቀ የቅዱስጊዮርጊስን ማሊያ የለበሱ ደጋፊዎች የእለቱን ዋና ዳኛ በቃላት የማይገለፅ አጅግ ፀያፍ ስድብ በተደጋጋሚ ከመሳደብ አልፈው ምራቃቸውን መትፋታቸውን በእለቱ ዋና ዳኛና የጨዋታ ታዛቢ ሪፖርት ቀረቦባቸዋል።
ከዚህም በተጨማሪ የተወሰኑ በቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ውስጥ የተለያዩየስራ ድርሻ ያላቸው ግለሰቦች ዳኞችንና የውድድር መሪዎችን ከመሳደብ አልፈው ከአወዳዳሪ አካላት ጋር ለድብድብ ሲጋብዙና ፀብ የሚያነሳሳድርጊቶችን ሲፈጽሙ እነደነበር በውድድር አመራሮች ሪፖርት ተደርጓል።
በዚህም መነሻነት የውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ በክለቡ ላይ የሚከተሉትን የቅጣት ውሳኔዎች አስተላልፏል።
1.የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ የሚያደርጋቸውን ቀጣይ 3 /ሶስት/ ጨዋታዎች ካለደጋፊ እንዲያካሂድ
2.በፋሲል ከነማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታ ላይ በደጋፊነት ተመዝግበው ውድድሩን እንዲመለከቱ የተፈቀደላችው 10/አስር/ ደጋፊዎች በዚህየውድድር ዘመን ሁሉንም ጨዋታዎች ወደ ስታድየም በመግባት እንዳይመለከቱ ታግደዋል
3.በቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ዉስጥ የተለያዩ የስራ ድርሻ ያላቸው ሰራተኞች አቶ ካሳሁን ደርበው /የሚድያ ባለሞያ/ እና አቶ ተስፋዬ ምንዳዬ /የሰው ሃብት አስተዳደር / ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ በሚያደርጋቸው ቀጣይ ተከታታይ የአምስት ሳምንት ውድድሮች ላይ ወደ ስታድየም በመግባት ጨዋታዎችንእንዳይመለከቱ የታገዱ መሆናቸዉን እያሳወቅን የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ከላይ ከ1-3 የተጠቀሱት ተግባራዊ እንዲሆኑ በሃላፊነት እንዲያስፈፅምና በቀጣይም ከመሰል ድርጊቶች እንዲቆጠቡ ሃላፊነቱን በአግባቡ እንዲወጣ ኮሚቴው በጥብቅ ያሳስባል።