መከላከያ ሶስት ተጫዋቾችን አስፈርሟል !!
ከቀጣዩ የዉድድር አመት አንስቶ መጠሪያዉን ወደ ቀደመ ስሙ መቻል የሚቀይረዉ መከላከያ ከሰአታት በፊት የሶስት ተጫዋቾችን ዝዉዉር ማጠናቀቁ ተረጋግጧል።
የመጀመሪያዉ ፈራሚ መከላከያ ያመራዉ ተጫዋቾች ደግሞ ከመከላከያ ወጣት ቡድን ከተገኘ ቡኋላ ከዚህ ቀደም ለባህርዳር ከተማ ፣ መቀለ 70 እንደርታ እና ወላይታ ዲቻ መጫዎት የቻለዉ አጥቂዉ ምንይሉ ወንድሙ ሆኗል።
ሌላኛዉ እና ሁለተኛው ፈራሚ ደግሞ የዉድድር አመቱን በሰበታ ከተማ ማሳለፍ የቻዉ እና ከዚህ ቀደም ለመቀሌ 70 እንደርታ ፣ መከላከያ እንዲሁም ወሌቂጤ ከተማ መጫወት የቻለዉ የመስመር ተጫዋቹ ሳሙኤል ሳሊሶ አሁን ደግሞ ወደ ቀድሞ ቤቱ መከላከያ መመለሱ ተረጋግጧል።
- ማሰታውቂያ -
በመጨረሻም ሶስተኛ ፈራሚ በመሆን ለክለቡ ፊርማዉን ያኖረዉ ደግሞ በዉድድር አመቱ በሀይቆቹ ቤት መድመቅ የቻለዉ ወጣቱ የግብ ዘብ ዳግም ተፈራ ሆኗል።
በተያያዘም ሶስቱም ተጫዋቾች ለሁለት አመት የሚቆይ የኮንትራት ዉል መፈራረማቸውን ለማረጋገጥ ችለናል።