ሀትሪክ ስፖርት ከቀናት በፊት ያስነበበቻችሁ የአጥቂው ዜና እውን ሆኗል።
አርባምንጭ ከተማ ሁለት ተጫዋቾችን ለማስፈረም በመከራ ላይ እየመለከተ እንደነበር ከቀናት በፊት ቀደም ብለን መዘገባችን ይታወሳል። ከእነኚህም ተጫዋቾች አንዱ የነበረው አጥቂው ፍቃዱ አለሙ እስከ ሰኔ ወር መጨረሻ አዞዎቹን ተቀላቅሏል።
የቀድሞው የአዲስ አበባ ከተማ ፣ መቻል ፣ አራት አመታትን ደግሞ በፋሲል ከነማ ያሳለፈው እንዲሁም ያለፈውን አመት በኢትዮ ኤሌክትሪክ የነበረው አጥቂው ፍቃዱ አለሙ ጥቂት ጊዜን በዕረፍት ካሳለፈ በኋላ አርባምንጭን ተቀላቅሏል።



