በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን የሊጉ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ በመሆን ያጠናቀቀው ዓሊ ሱሌማን ወደ ግብፅ በማምራት አዲስ ክለብ ተቀላቅሏል።
ኤርትራዊው ተጫዋች ካህራባ እስማይልያ ለተሰኘ ክለብ ከደቂቃዎች በፊት ፊርማውን አኑሯል።
ከተመሰረተ 90 ዓመታት ያስቆጠረው ካህራባ እስማይልያ ክለብ በቀጣዩ የውድድር ዘመን በግብፅ ፕሪሚየር ሊግ ይሳተፋል።
በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ለባህርዳር ከተማ እና ሀዋሳ ከተማ የተጫወተው ዓሊ ሱሌማን በ2016 እና በ2017 የሊጉ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ሆኖ ማጠናቀቁ ይታወቃል።
- ማሰታውቂያ -



