ኮትዲቯር ሌላ ወሳኝ ተጫዋቻቸውን ለማጣት ተቃርበዋል

ከሀገሪቱ የመገናኛ ብዙሀን በዛሬው ዕለት እየወጡ በሚገኙ መረጃዎች ኮትዲቯር በመጪው ቀናት ከ ኒጀር እና ከ ዋልያዎቹ ጋር ላለባቸው ወሳኝ ጨዋታ ያለ አምበላቸው ሰርጂ ኦሪየር ጨዋታቸውን ሊያካሂዱ እንደሚችሉ ተጠቁሟል ።

ሰርጂ ኦሪየር በትላንትናው እለት ክለቡ በሊጉ በነበረው ጨዋታ ያልተሰለፈ ሲሆን የቶተንሀም የኮምኒኬሽን ክፍል ኦሪየር በህመም ምክንያት አለመሰፉን በመግለፅ ተጨማሪ ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዋል ።

የኮትዲቯር የእግር ኳስ ፌዴሬሽን በጉዳዩ ላይ ይፋ ያደረገው ነገር ባይኖርም በትላንትናው ዕለት የአጥቂያቸውን ሴባስቲያን ሀለር በኮሮና መያዝ ይፋ አድርገዋል ።

በተያያዘ ዜና ከደቂቃዎች በፊት በወጣ መረጃ የኮትዲቯር ዋና አሰልጣኝ ፓትሪክ ቢምዬሌ በማልሪያ በሽታ መታመማቸው ሲገለፅ በዛሬው ዕለት አመሻሽ ላይ ብሔራዊ ቡድኑን ልምምድ እንደሚያሰሩ ተገልጿል ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor