መነሻ ገጽ አፍሪካ ከምሽቱ ጨዋታ አስቀድሞ ስለሁለቱ ሀገራት የአፍሪካ ዋንጫ ታሪክ አስገራሚ ቁጥሮች !!
አፍሪካአፍሪካ ዋንጫዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

ከምሽቱ ጨዋታ አስቀድሞ ስለሁለቱ ሀገራት የአፍሪካ ዋንጫ ታሪክ አስገራሚ ቁጥሮች !!

አጋራ
አጋራ

ከስምንት አመታት በኋላ በአሰልጣኝ ዉበቱ አባተ እየተመሩ በአፍሪካ ዋንጫው ላይ ለመሳተፍ ከሁለት ሳምንታት በፊት ወደ አዘጋጇ ሀገር ካሜሩን ያቀኑት ዋልያዎቹ በዛሬው ዕለት ምሽት 4:00 ሰዓት ላይ የመጀመሪያ የምድብ ጨዋታቸውን ከኬፕ ቨርዴ ጋር የሚያደርጉ ይሆናል።

ከምሽቱ ተጠባቂ ጨዋታ አስቀድሞም የሁለቱ ሀገራት ብሔራዊ ቡድኖችን ከአፍሪካ ዋንጫው ጋር ተያይዞ ያላቸዉን ጥቂት ቁጥራዊ መረጃዎች እንዲህ አቅርበናቸዋል።

በአፍሪካ ዋንጫዉ ኢትዮጵያ እና ኬፕ ቨርዴ ዛሬ ምሽት ለመጀመሪያ ጊዜ የሚገናኙ ይሆናል።

ከግብፅ እና ሱዳን ጋር በመሆን የመጀመሪያውን የአፍሪካ ዋንጫ ከመሰረቱት እንዲሁም በውድድሩ ላይ ከተሳተፉ ሶስት ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ ናት።

በመድረኩ ላይ የዋልያዎቹ ትልቅ ዉጤት በ1962 ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫዉን ማንሳት መቻላቸው ነዉ።

ባለፋት 20 አመታትም የኢትዮጵያ ብሔራ ቡድን ለሁለተኛ ጊዜ በመድረኩ ላይ መሳተፍ ችለዋል።

ዋልያዎቹ ይህ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፏቸው ለአስራ አንደኛ ጊዜ ነዉ።

ኢትዮጵያ ከሀገሯ ውጪ ካደረገቻቸው 17 የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታዎች አንዱን ብቻ ማሸነፍ ስትችል ሁለቱን አቻ ወጥታ አስራ አራት ጊዜ ደግሞ ተሸንፋለች።

ያሸነፈችዉ ብቸኛ ጨዋታም በ1963 ቱኒዚያን 4-2 በሆነ ዉጤት ነበር።

የዋልያዎቹ አጥቂ እና የምንግዜም የብሔራዊ ቡድኑ ከፍተኛ ግብ አግቢ የሆነው ጌታነህ ከበደ ለሁለተኛ ጊዜ በመድረኩ ለይ የተገኘ ሲሆን፤ በ2013 የደቡብ አፍሪካዉ የአፍሪካ ዋንጫ ላይ 189 ደቂቃዎችን በሜዳ ላይ አሳልፎ አንድም ኢላማውን የጠበቀ የግብ ሙከራ ማድረግ አልቻለም ነበር።

ዋልያዎቹ 26 ተጫዋቾችን ከሀገር ዉስጥ ሊግ የመረጡ ሲሆን ሁለት ተጫዋቾች ብቻ ከአፍሪካ ሊጎች አካተዋል ። (ሙጅብ ቃሲም እና ሽመልስ በቀለ)

በተጨማሪም ዋልያዎቹ በፊፋ የታህሳስ ወር ደረጃ 137ኛ ላይ ትገኛለች።

በኬፕ ቨርዴ በኩል ደግሞ :-

ኬፕ ቨርዴ በአፍሪካ ዋንጫዉ ስትሳተፍ ይህ ለሶስተኛ ጊዜ ሲሆን ሶስቱም ተሳትፎዋ ከ2013 በኋላ ነዉ።

በተሳተፋባቸዉ የአፍሪካ ዋንጫ ዉድድሮችም እስከአሁን ካደረጉት 7 ጨዋታዎች አምስቱን በአቻ ውጤት ያጠናቀቁ ሲሆን ብቸኛዉ ድላቸው አንጎላን በ2013 የምድብ ጨዋታ ላይ 2ለ1 የረቱበት ነዉ።

ኬፕ ቨርዲዎች በአፍሪካ ዋንጫዉ ካደረጓቸው ሰባት ጨዋታዎች መካከልም በአንዱ ብቻ ከሁለት ጎል በላይ ማስቆጠር ችለዋል።

ኬፕ ቨርዴዎች በመድረኩ ትልቁ ዉጤታቸዉ በ2013 ሩብ ፍፃሜ የደረሱበት ነበር።

ኬፕ ቨርዴ ከመረጠቻቸዉ 26 ተጫዋቾች መካከል ሀያ አምስቱ ከሀገር ዉጭ ሊግ የሚጫወቱ ሲሆን 1 ተጫዋች ማለት ግብ-ጠባቂያቸውን ብቻ ከሀገር ዉስጥ ሊግ አካተዋል።

በተጨማሪም ኬፕ ቨርዴ በፊፋ የታህሳስ ወር ደረጃ 73ኛ ላይ ተቀምጣለች።

የሁለቱ ሀገራት ተጠባቂ ጨዋታም ምሽት 4:00 ሰዓት ላይ በያዉንዴ ኦሊምቢ ስታዲየም የሚደረግ ይሆናል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

  • I like your evidence-based comparison. Thank you, Brother. Keep it up! I am also a member of the Telegram Group.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...