ከምሽቱ የዋልያዎቹ እና የኬፕ ቨርዴ ጨዋታ በኋላ የአሰልጣኞች አስተያየት

በአፍሪካ ዋንጫው የመክፈቻ ዕለት ሁለተኛ ጨዋታ ኬፕ ቨርዴ ዋልያዎቹን በጠባብ ዉጤት ማሸነፍ የቻሉ ሲሆን ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ አሰልጣኞች ተከታዮቹን አስተያየቶች ሰጥተዋል።

ሁምቤርቶ ቤቴንኮርት (የኬፕ ቨርዴ ም/አሰልጣኝ)

በመጀመሪያ ይህንን ድል ለዚህ ቶታል ኢነርጂ AFCON የማጣሪያ ዉድድር ተሳታፊ ለነበሩት እና መምጣት ላልቻሉ ተጫዋቾቻችን እና የቴክኒክ ባለሙያዎች በሙሉ መስጠት እወዳለሁ። እንዲሁም እኛን ለሚደግፉልን ለሁሉም የኬፕ ቨርዳውያን ሰጥቻቸዋለሁ።

ወደ ሚቀጥለው ዙር ለመሻገር የሚረዳንን ወሳኝ ሶስት ነጥብ ነዉ በዛሬዉ ጨዋታ ማሳካት የቻልነዉ። የኢትዮጵያ ቡድንን ጥራት እናውቅ ነበር ይህም በጨዋታው ወቅት ረድቶናል መሀል ሜዳ ላይ ያሉትን ክፍተቶች ተጠቅመን የተሻለውን ኳስ ተጫውተን አሸንፈን መዉጣት ችለናል።

ዉበቱ አባተ (የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ )

” እንዴ ኬፕ ቨርዴዎች ጥሩ ለመጨዋወት ያን ያህል ልምድ አልነበረንም። ሽንፈቱን ተቀብለናል ለቀጣይ ጨዋታዎቻችን ከዛሬዉ ጨዋታ የምንማረዉ ነገር ይኖራል።

አብዝሀኛዉን የጨዋታ ሰዓት በጎዶሎ ተጫዋች ነዉ የተጫወትነው ይሄ እኛን በጣም ጎድቶናል። ለተጋጣሚያችን ግን የተመቸ ነበር በተለይ በአካል ብቃቱ ረገድ ረድቷቸዉ አሸንፈዉናል።

Writer at Hatricksport

Facebook

Ermias Misganaw

Writer at Hatricksport

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *